1ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ 2በቅንነት የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፤ 3ከሰነፎች አፍ የስድብ በትር ይወጣል፤ 4በሬዎች በሌሉበት ስፍራ በረቱ ንጹሕ ነው፤ 5የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ 6በክፉዎች ዘንድ ጥበብን ትፈልጋለህ፥ አታገኛትምም፤ 7በሰነፍ ሰው ፊት ሁሉ ጠማማ ነው፥ 8የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ 9የኃጥኣን ቤቶች መንጻትን ይሻሉ፥ 10የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ 11የክፉዎች ቤቶች ይፈርሳሉ፤ 12በሰዎች ዘንድ ቅን የምትመስል መንገድ አለች፤ 13ከደስታ ጋር ኀዘን አይቀላቀልም፥ 14ልበ ትዕቢተኛ ከራሱ መንገድ ይጠግባል። 15የዋህ ነገርን ሁሉ ያምናል፤ 16ብልህ ሰው ፈርቶ ከክፉ ይሸሻል፤ 17ቍጡ ሰው ያለምክር ይሠራል፤ 18አላዋቂዎች ሰዎች ክፋትን ይካፈላሉ፤ 19ክፉዎች በደጎች ፊት ይሰነካከላሉ፥ 20ባለጠጎች ወዳጆች ድሆች ወዳጆችን ይጠላሉ፤ 21ድሃውን የሚንቅ ኀጢአትን ይሠራል፤ 22ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ 23በሁሉ ነገር ጠንቃቃ ለሆነ ብዙ ትርፍ አለው። 24ዐዋቂ ሰው የጠቢባን ዘውድ ነው፤ 25እውነተኛ ምስክር ነፍስን ከክፉ ያድናል፥ 26እግዚአብሔርን ለሚፈራ ጽኑዕ ተስፋ አለው፥ 27የእግዚአብሔር ትእዛዝ የሕይወት ምንጭ ነው። 28የንጉሥ ክብር በሕዝብ ብዛት ነው፤ 29ትዕግሥተኛ ሰው ጥበብ የበዛለት ይሆናል፤ 30የሚያስታርቅ ሰው የልብ ፈዋሽ ነው፤ 31ድሃን የሚያስጨንቅ ፈጣሪውን ያስቈጣዋል፤ 32ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ 33በደግ ሰው ልብ ጥበብ ታድራለች፤ 34ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ 35አስተዋይ መልእክተኛ በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ነው፤