1ዐዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሣጽ ይሰማል፤ 2ደግ ሰው ከጽድቅ ፍሬ መልካምን ይበላል፤ 3አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ 4የማይሠራ ሁሉ በምኞት ይኖራል። 5ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ 6መንገዳቸው ቀና የሆነውን የዋሃንን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፤ 7ምንም ሳይኖራቸው ራሳቸውን ባለጠጎች የሚያደርጉ አሉ፥ 8ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ 9ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ 10ክፉ ሰው ከመሳደብ ጋር ክፋትን ይሠራል፤ 11በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ 12ከሚበለጽግና በተስፋ ከሚቈይ ሰውነቱን ሊረዳ የሚጀምር ይሻላል። 13የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ 14የብልህ ሰው ሕግ የሕይወት ምንጭ ነው። 15መልካም ዕውቀት ሞገስንና ጥበብን ይሰጣል፤ 16ብልህ ሁሉ በዕውቀት ይሠራል፤ 17ሰነፍ መልእክተኛ በክፉ ላይ ይወድቃል፤ 18ትምህርት ድህነትንና ጕስቍልናን ያስወግዳል፤ 19የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ 20ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ 21በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ 22ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ 23ጻድቃን ለብዙ ዓመት በብልጽግና ይኖራሉ፤ 24በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፤ 25ጻድቅ ሰውነቱ እስክትጠግብ ድረስ ይበላል፤