1ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ 2የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል። 3ከዐመፃ የማይርቅ ሰው ይጠፋል፤ 4ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ 5የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፤ 6የኃጥኣን ምክር ተንኮል ነው። 7ኀጢአተኛ በተገለበጠበት ይጠፋል፥ 8የብልህ ሰው አንደበት በሰው ሁሉ ዘንድ ይመሰገናል፤ 9ለራሱ ባሪያ ሆኖ የተጠቃ ሰው 10ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ 11ምድሩን የሚያርሳት ሰው እንጀራን ይጠግባል፤ 12የኃጥኣን ምኞት ክፋት ናት። 13ኀጢአተኛ ሰው በከንፈሩ ኀጢአት ወደ ወጥመድ ይወድቃል፤ 14የሰው ነፍስ ከአፉ ፍሬ መልካም ነገርን ትጠግባለች፥ 15የሰነፎች መንገድ በፊታቸው የቀናች ናት፤ 16ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ 17ጻድቅ ሰው የተገለጠ እውነትን ያስተምራል፤ 18በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ 19የጻድቃን ከንፈሮች ምስክርነትን ያቀናሉ፥ 20ክፉን በሚያስብ ልብ ውስጥ ማታለል አለ፤ 21ጻድቅን ምንም ክፉ ነገር ደስ አያሰኘውም፤ 22ሐሰተኛ ከንፈር በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ 23ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ 24የተመረጡ ሰዎች እጅ ፈጥኖ ይገዛል፤ 25የሚያስደነግጥ ቃል የጻድቅ ሰው ልቡናን ያውካል፤ 26ራሱን የሚያውቅ ሰው ለራሱ ጻድቅ ነው፤ 27ታካች ሰው አድኖ አይዝም። 28በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥