1አባይ ሚዛን በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው፤ 2ትዕቢት ባለበት በዚያ ውርደት አለ፤ 3ጻድቃንን ፍጻሜያቸው ትመራቸዋለች፤ 4በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ 5የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ 6ቅኖች ሰዎችን ጽድቃቸው ይታደጋቸዋል፤ 7ጻድቅ ሰው በሞተ ጊዜ ተስፋውን አያጣም፥ 8ጻድቅ ከወጥመድ ያመልጣል፥ 9በክፉዎች አፍ የሀገር ወጥመድ አለ፥ 10በጻድቃን ደግነት ከተማ ትቀናለች፥ 11በቅኖች በረከት ከተማ ከፍ ከፍ ትላለች፤ 12ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። 13ሁለት ምላስ የሆነ ሰው የጉባኤን ምሥጢር ይገልጣል፤ 14መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። 15ክፉ ሰው ከጻድቅ ጋር በተቀላቀለ ጊዜ ይከፋል፥ 16ደግ ሴት ለባሏ ክብርን ታስገኛለች፥ 17ቸር ሰው ለነፍሱ መልካም ያደርጋል፤ 18ክፉ ሰው የበደልን ሥራ ይሠራል፤ 19ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ 20ጠማማ መንገድ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ 21በሐሰት እጅን በእጅ የሚመታ አይድንም፤ 22የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥ 23የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ 24የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤ 25የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ 26ስንዴውን የሚያደልብ ለአሕዛብ ይተወዋል። 27መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል። 28በባለጠግነቱ የሚተማመን ሰው ይወድቃል፤ 29ቤቱን የማያውቅ ሰው ነፋስን ይወርሳል፥ 30ከጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ይወጣል። 31እነሆ፥ ጻድቅ በምድር ላይ በጭንቅ የሚድን ከሆነ፥