ልዩ ልዩ የሰሎሞን ምሳሌዎች
1ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ 2የሀብት ድልብ ለኃጥኣን አይጠቅምም፤ 3እግዚአብሔር ጻድቅት ነፍስን አያስርብም፤ 4የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ 5የተማረ ልጅ ብልህ ይሆናል። 6የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ነው። 7የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። 8በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ 9በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ 10ለክፋት በዐይኑ የሚጠቃቀስ ለሰው ኀዘንን ይሰበስባል፥ 11የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ 12ቍጣ ጥልን ያነሣሣል። 13ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ 14ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ 15የባለጠጋ ሀብት የጸናች ከተማ ናት፤ 16የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ 17ተግሣጽ የሕይወትን መንገድ ይጠብቃታል፤ 18ልዝብ ከንፈሮች ጥልን ይሸፍናሉ፤ 19ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ 20የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ 21የጻድቃን ከንፈሮች የሩቁን ያውቃሉ፤ 22የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ 23ሰነፍ ሰው በመሳቁ ክፉን ይሠራል፤ 24ኃጥእ ወደ ጥፋት ይመለሳል፥ 25ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ 26ጨርቋ ለጥርስ፥ ጢስም ለዐይን ጎጂ እንደ ሆነ፥ 27እግዚአብሔርን መፍራት ዘመንን ያረዝማል፤ 28ደስታ ከጻድቃን ጋር ትኖራለች፤ 29እግዚአብሔርን መፍራት ለደግ ሰው ብርታት ነው፥ 30ጻድቃን ለዘለዓለም አይናወጡም፤ 31የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ 32የጻድቃን ከንፈሮች ሞገስን ያፈስሳሉ፤