የኢዮብ መልስ
1ኢዮብም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦ 2“ከእናንተ አንዱ መቅሠፍቴን ምነው በመዘነ ኖሮ! 3ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና፤ 4እነሆ፥ የእግዚአብሔር ፍላጻ በሥጋዬ ላይ ነው፤ 5በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በከንቱ ይጮኻልን? የሚበላውን ፈልጎ አይደለምን? 6ምግብ ያለ ጨው ይበላልን? 7ሰውነቴ ማረፍ አልቻለችም፤ 8ልመናዬ ምነው በደረሰልኝ! 9እግዚአብሔርም ያቈስለኝ ዘንድ ጀመረ፥ 10መቃብሬ በግንቡ የምመላለስበት ከተማዬ ይሁን፥ 11እታገሥ ዘንድ ጕልበቴ ምንድን ነው? 12ጕልበቴ የድንጋይ ጉልበት ነውን? 13በእርሱ የታመንሁ አይደለሁምን? 14ምሕረቱ ቸል አለኝ፥ 15“ወንድሞቼም እንደ ደረቅ ወንዝ፥ 16ያከብሩኝ የነበሩ እነዚያ፥ 17ወደ ሙቀት ሲቀርብ በቀለጠ ጊዜ 18እንደዚሁም እኔ ከሁሉ ተለይቼ ጠፋሁ፥ 19የቴማናውያንን መንገዶች፥ 20በከተሞችና በገንዘቦች የሚታመኑ ያፍራሉ። 21አሁንም እናንተ ያለ ምሕረት መጣችሁ፤ 22ለምን? በውኑ፦ ከእናንተ አንዳች ነገር ጠየቅሁን? 23ወይስ ከጠላቶች እጅ ታስጥሉኝ ዘንድ 24“አስተምሩኝ፥ እኔም አዳምጣችኋለሁ፤ 25የእውነተኛ ሰው ቃል ሐሰትን ይመስላል፥ 26የንግግራችሁም ማጽናናት ዕረፍትን አይሰጠኝም፤ 27በድሃ አደጉ ላይ ትስቃላችሁና፥ 28አሁንም፥ ፊታችሁን አይቼ 29አሁንም ተቀመጡ፤ በደልም አይኑር፤ 30በአንደበቴ በደል የለምና