ኤልዩስ ኢዮብን እንደ ገሠጸው
1“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥ 2እነሆ፥ አፌን ከፍቻለሁ፥ 3ልቤም ንጹሕ ነገርን ያስባል፥ 4የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ 5በዚህ ነገር ልትመልስልኝ ትችል እንደ ሆነ ታገሠኝ፥ 6አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተፈጠርህ ነህ፥ 7እነሆ፥ ግርማዬ አታስፈራህም፥ 8ግፍህን ተናግረሃል፥ 9እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አልበደልሁምና፤ 10እነሆ፥ ምክንያት አግኝቶብኛል፥ 11እግሬን በግንድ አጣበቀ፥ 12እነሆ፥ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ቃሌንም አይሰማኝም እንዴት ትላለህ? 13አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይሰማኝም?’ ትላለህ። 14እግዚአብሔር በሕልም ወይም በሌሊት ራእይ፥ 15በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ 16በዚያን ጊዜ የሰዎችን ማስተዋል ይከፍታል፥ 17ሰውን ከኀጢአቱ ይመልሰው ዘንድ፥ 18ነፍሱን ከሞት ያድናታል፤ 19“ደግሞ በአልጋ ላይ በደዌ ይገሥጸዋል፥ 20ማንኛውንም መብል መቅመስ አይችልም። 21ሥጋው እስከሚያልቅ ድረስ፥ 22ሰውነቱ ለሞት፥ 23የሞት መላእክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥ 24በሞት እንዳይጠፋ ይጠብቀዋል፥ 25ሥጋውን እንደ ሕፃን ሥጋ ያለመልማል፤ 26ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ 27ያንጊዜም ሰው ራሱን ይነቅፋል፤ እንዲህም ይላል፦ 28ነፍሴ ወደ ጥፋት እንዳትወርድ አድኖአታል፥ 29“እነሆ፦ ሁሉን የሚችል እርሱ፥ 30ሕይወቴም በብርሃን ውስጥ ታመሰግን ዘንድ፥ 31ኢዮብ ሆይ፥ አድምጥ፥ እኔንም ስማ፤ 32ነገር ቢኖርህ ተናገር፤ 33ያለዚያም እኔን ስማ፤