1ኢዮብም በፊታቸው ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ወዳጆቹ ለኢዮብ ለመመለስ ዝም አሉ። 2ከአውስጢድ ሀገር ከአራም ወገን የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊዩስ ተቈጣ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና ኢዮብን ተቈጣው። 3ደግሞም እንደ ኀጢአተኛ አደረጉት እንጂ ለኢዮብ የሚገባ መልስ መመለስ ስላልቻሉ በሦስቱ ባልንጀሮቹ ላይ ተቈጣ። 4ኤሊዩስ ግን ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ለኢዮብ መልስ ለመስጠት ጠብቆ ነበር። 5ኤሊዩስም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ባየ ጊዜ በቍጣው ተቈጣቸው። 6የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፥ “እኔ በዕድሜዬ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ዕውቀቴን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈርቼ ዝም አልሁ። 7እንደዚህም አልሁ፥ “የሚናገሩ ዓመታት አይደሉም፥ 8ነገር ግን በሟች ሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ 9በዕድሜ ያረጁ ጠቢባን አይደሉም፥ 10ነገር ግን፦ ስሙኝ፤ 11እነሆ፥ ንግግሬን አድምጡኝ፤ 12እንዲሁም ልብ አደረግሁ፤ 13እናንተም፦ ከእግዚአብሔር ጥበብን አግኝተናል፤ 14እናንተ ግን እንዲህ ያለ ነገር እንዲናገር 15“እናንተ ፈራችሁ፥ ዳግመኛም አልመለሳችሁም፤ 16እኔ በትዕግሥት ጠበቅሁ እንጂ አልተናገርሁም። 17ኤልዩስም መለሰ፥ እንዲህም አለ፦ 18እኔ ቃል ተሞልቻለሁና፥ 19በተሃ ጠጅ እንደ ተሞላና ሊቀደድ እንደ ቀረበ አቁማዳ፥ 20ጥቂት እንድተነፍስ እናገራለሁ። 21ከሰው የተነሣ አላፍርምና፥ 22ለሰው ፊት ማድላትን አላውቅም፤