የበልዳዶስ ንግግር
1አውኬናዊው በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦ 2“ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? 3ስለ ምንስ እንደ እንስሳ በፊትህ ዝም አልን? 4መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው? 5“የኀጢኣተኞች መብራት ይጠፋል፥ 6ብርሃኑ በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፤ 7የተዋረዱ ሰዎች ንብረቱን ይወስዳሉ፤ 8እግሩ በወጥመድ ትያዛለች፤ 9አሽክላዎች በላዩ ይመጣሉ፤ 10በምድር ላይ የሸምቀቆ ገመዱ ተሰውራለች፤ 11መከራ በዙሪያው ታጠፋዋለች፤ 12ኀይሉ በራብ ትደክማለች። 13ጭኖቹ ይበሰብሳሉ። 14ጤንነት ከሥጋው ትርቃለች። 15በሌሊት በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፤ 16ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፤ 17መታሰቢያውም ከምድር ይጠፋል፤ 18ከብርሃን ወደ ጨለማ አርቀው ያፈልሱታል። 19ከሕዝቡ መካከል የሚራራለት የለም፤ 20ነገር ግን ባዕድ በንብረቱ ላይ ተድላ ያደርጋል፤ 21የኀጢኣተኞች ቤት እንዲህ ነው፤