1“ነፍሴ ስለ ተጨነቀች 2እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ 3ኀጢኣተኛ ብሆን በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? 4በውኑ የሰው ዐይን አለህን? 5ዘመንህ እንደ ሰው ዘመን ነውን? 6ክፋቴን ትፈላለግ ዘንድ፥ 7ከዚህ በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ አንተ ታውቃለህ። 8“እጆችህ ፈጠሩኝ፤ ሠሩኝም፤ 9ከጭቃ እንደ ፈጠርኸኝ አስብ፤ 10በውኑ እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? 11ቍርበትና ሥጋን አለበስኸኝ፤ 12ሕይወትና ቸርነትን ሰጠኸኝ። 13ይህ ሁሉ በአንተ ዘንድ አለ። 14ኀጢኣት ብሠራ አንተ ትጠባበቀኛለህ፤ 15በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ 16ለመገደል እንደ አንበሳ ታደንሁ። 17ዳግመኛም ከጥንት ጀምሮ ትመረምረኛለህ፤ 18“ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? 19እንዳልነበረስ ለምን አልሆንሁም? 20የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? 21ወደማልመለስበት ስፍራ፥ 22የዘለዓለም ጨለማም ወደ አለባት፥