1በፍጥረታት ሁሉ ላይና በከዋክብት ሁሉ ላይ የተሾሙ የሻለቆችን የሚመሩ፥ እንደ ዘመኑ ቍጥር ሁሉ ከሚጨመርባቸውና ከመኖሪያቸው ጋር ከማይለዩት ከአራቱ ከዋክብት ጋር 2እነዚህም፥ በዓመቱ ቍጥር የማይቈጠሩ አራቱን ቀኖች 3እነዚያ ከዋክብት ዓለም ጸንቶበት በሚኖረው ዘመን በእውነት ይገዛሉና ሰዎች በእነርሱ ይበድላሉ። 4አንዱ በመጀመሪያው መስኮት 5ለምልክት 6በዚህ ዓለም በሰማይ ያበሩ ዘንድ፥ በምድርም ላይ ይታዩ ዘንድ፥ 7ፀሐይና ጨረቃ፥ ከዋክብትም፥ በሰማይ ሠረገላዎች ሁሉ የሚዞሩ ቅንየታት የሚባሉ ኮከቦችም ሁሉ ለመዓልትና ለሌሊት መሪዎች ይሆኑ ዘንድ፥ 8ዑርኤል በሰማይ ፀሐይ በሚመላለስባቸው በሠረገላዎች ዙሪያ የፀሐይ እግሮች ከእነርሱ የሚወጡባቸው የተከፈቱ ዐሥራ ሁለት መስኮቶችን እንዲህ አሳየኝ። 9በታወቁባቸው ዘመኖችም በተከፈቱ ጊዜ ከእነርሱ በምድር ላይ ድርቅ ይወጣል። 10ለነፋሳትና ጠልን ለሚያመጣ ነፋስ በዘመኖች በተከፈቱ ጊዜ በምድር ዳርቻ በሰማይ ሆኜ ፀሐይና ጨረቃ፥ ከዋክብትም፥ የሰማይ ፍጥረቶችም ሁሉ በምሥራቅና በምዕራብ ከእነርሱ የሚወጡባቸው የተከፈቱ ዐሥራ ሁለት መስኮቶችን በምድር ዳርቻ ባለ በሰማይ አየሁ። 11ብዙ የተከፈቱ መስኮቶችም ከቀኙና ከግራው አሉ። 12ጌታ እንዳዘዛቸው ከዋክብት ከእነርሱ እንደሚወጡባቸው፥ እንደ ቍጥራቸው መጠን፥ እንደሚገቡባቸውም እንደ እነዚያ መስኮቶች አንዲቱ መስኮት በዘመኗ ሙቀትን ታስገኛለች። 13የማይገቡ ከዋክብት በሚመላለሱባቸው በእነዚያ መስኮቶች በበላያቸውና በበታቻቸው ሠረገላዎችን ለዘለዓለም በሰማይ ሲሮጡ አየሁ። 14ሁሉንም አንዱ