1የሰማይ ብርሃናትን መመላለስ የሚናገር መጽሐፍ። 2እየአንዳንዳቸው በየወገናቸው እንደ አሉ፥ እየአንዳንዳቸውም በየሥልጣናቸውና በየዘመናቸው፥ እየአንዳንዳቸውም በየስማቸውና በየመውጫቸው፥ በየወራታቸውም ከእኔ ጋር ያለው መሪያቸው መልአክ ቅዱስ ዑርኤል እንደ አሳየኝ። 3ሰሌዳቸውንም ሁሉ፥ ዓመተ ዓለምን እስከ ዘለዓለም ድረስ፥ እስከ ዘለዓለም የሚኖር ሐዲስ ሥራም እስኪሠራ ድረስ እርሱ እንዳሳየኝ። 4የብርሃናት መጀመሪያ ትእዛዝ ይህ ነው። 5ፀሐይ ብርሃን ነው፤ መውጫውም በምሥራቅ በኩል በሰማይ መስኮቶች ነው፤ መግቢያውም በምዕራብ በኩል በሰማይ መስኮቶች ነው። 6ፀሐይ የሚወጣባቸው ስድስት መስኮቶችን አየሁ፤ ፀሐይ የሚገባባቸውን ስድስት መስኮቶችንም አየሁ። 7ጨረቃም በእነዚያ መስኮቶች ይወጣል፤ ይገባልም። 8የሰማይ ከዋክብትን የሚመሩም ከሚመሯቸው ጋር፥ ስድስቱ በምሥራቅ፥ ስድስቱም በፀሐይ መግቢያ ናቸው። 9ሁሉም እየአንዳንዱ ከሌላው በኋላ የቀና ነው፤ በዚያም መስኮት በቀኙና በግራው ብዙ መስኮቶች አሉ። 10መጀመሪያ ስሙ ፀሐይ የሚባል ታላቁ ብርሃን ይወጣል፤ ዙሪያውም እንደ ሰማይ ዙሪያ ነው፤ ሁለመናውም የሚያበራና የሚያቃጥል እሳትን የተመላ ነው። 11የሚሄድባቸውንም ሠረገላዎች ነፋስ ይነዳቸዋል። 12ፀሐይም ከሰማይ ይጠልቃል፤ ወደ ምሥራቅም ይሄድ ዘንድ ወደ መስዕ ይመለሳል፥ ወደዚያ መስኮት ይገባ ዘንድ ይመራል፤ በሰማይም ሆኖ ያበራል። 13እንደዚህ በመጀመሪያው ወር በታላቁ መስኮት ይወጣል፤ ፀሐይ በምሥራቅ ከሚወጣባቸው ከስድስቱ መስኮቶች በአራተኛዪቱ ይወጣል። 14በመጀመሪያው ወር ፀሐይ ከእርሷ በሚወጣባት በዚያች በአራተኛዪቱ ደጃፍም በዘመናቸው በሚከፈቱበት ጊዜ ከእነርሱ ዋዕይ የሚወጣባቸው ዐሥራ ሁለት ደጃፎች አሉባት። 15ፀሐይ ከምሥራቅ በወጣ ጊዜ በዚች በአራተኛዪቱ ደጃፍ ሠላሳ ቀን ይወጣል። 16በሰማይ በአለው መግቢያም በአራተኛዪቱ ደጃፍ አቅንቶ ይወርዳል። 17በእነዚያም ወራት እስከ ሠላሳ ቀን ድረስ ቀኒቱ ከቀን ትረዝማለች፤ ሌሊቲቱም ከሌሊት ታጥራለች። 18በዚችም ቀን ቀኒቱ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ትረዝማለች። 19ጠንቅቀውም ቢቈጥሯት ቀኒቱ ዐሥር ክፍል ትሆናለች፤ ሌሊቲቱም ስምንት ክፍል ትሆናለች። 20ፀሐይም ከዚች ከአራተኛዪቱ ደጃፍ ይወጣል፤ በአራተኛዪቱም ደጃፍ ይገባል። 21ሠላሳ ቀንም በምሥራቅ ወዳለችው ወደ አምስተኛዪቱ ደጃፍ ይመለሳል፤ ከእርሷም ይወጣል፤ በአምስተኛዪቱም ደጃፍ ይገባል። 22ያንጊዜም ቀኒቱ ሁለት እጅ ትረዝማለች፤ ቀኒቱም ዐሥራ አንድ ክፍልን ትሆናለች፤ ሌሊቲቱም ታጥራለች፤ ሰባት ክፍልንም ትሆናለች። 23ፀሐይም ወደ ምሥራቅ ይመለሳል፤ ወደ ስድስተኛዪቱም ደጃፍ ይገባል፤ ስለ እርስዋም ምልክት 24በዚያችም ቀን ቀኒቱ ከሌሊቲቱ ትረዝማለች፤ ቀኒቱም የሌሊቲቱን እጥፍ ትሆናለች፤ ቀኒቱም ዐሥራ ሁለት ክፍልን ትሆናለች። ሌሊቲቱም ታጥራለች፤ ስድስት ክፍልንም ትሆናለች። 25ቀኒቱም ታጥር ዘንድ፥ ሌሊቲቱም ትረዝም ዘንድ ፀሐይ ይነሣል። 26ፀሐይም ወደ ምሥራቅ ይመለሳል፤ ወደ ስድስተኛውም መስኮት ይገባል፤ ከእርስዋም ሠላሳ ቀን ይወጣል፤ ይገባልም። 27ሠላሳውም ቀን ከተፈጸመ በኋላ በጥንቃቄ ቢቈጠር ቀኒቱ አንድ ክፍል ትጐድላለች፤ ቀኒቱም ዐሥራ አንድ ክፍል ትሆናለች፤ ሌሊቲቱም ሰባት ክፍል። 28ፀሐይም ከስድስተኛዪቱ መስኮት ከምዕራብ ወጥቶ ወደ ምሥራቅ ይሄዳል፤ ሠላሳ ቀንም በአምስተኛዪቱ መስኮት ይወጣል፤ ዳግመኛም በምዕራብ በኩል በአለችው በአምስተኛዪቱ መስኮት በምዕራብ ይገባል። 29በዚያችም ቀን ቀኒቱ ሁለት ክፍል ታንሳለች፤ ቀኒቱም ዐሥር ክፍል ትሆናለች፤ ሌሊቲቱም ስምንት ክፍል ትሆናለች። 30ፀሐይም ከዚያች ከአምስተኛዪቱ መስኮት ይወጣል፤ በምዕራብ በኩል በአምስተኛዪቱ መስኮት ይገባል። 31ስለ እርስዋ ምልክትም 32በዚያችም ቀን መዐልቱ ከሌሊቱ ጋር ይስተካከላል፤ የተካከለም ይሆናል፤ ሌሊቲቱም ዘጠኝ ክፍል ትሆናለች። መዐልቱም ዘጠኝ ክፍል ይሆናል። 33ፀሐይም ከዚያች መስኮት 34በሦስተኛውም መስኮት ሠላሳ ቀን ይወጣል፤ በምዕራብም በሦስተኛዪቱ መስኮት ይገባል። 35በዚችም ቀን ሌሊቲቱ ከሌሊቲቱ እስከ ሠላሳ ቀን ትረዝማለች፤ ቀኒቱም ከቀኒቱ እስከ ሠላሳ ቀን ታጥራለች፥ በጥንቃቄ ቢቈጠርም ሌሊቱ ዐሥር ክፍል ይሆናል፤ ቀኑም ስምንት ክፍል ይሆናል። 36ፀሐይም ከዚያች ከሦስተኛዪቱ መስኮት ወጥቶ በምዕራብ በሦስተኛዪቱ መስኮት ይገባል፥ ወደ ምሥራቅም ይመለሳል። 37ፀሐይም በምሥራቅ በሁለተኛው መስኮት ሠላሳ ቀን ይወጣል። 38እንደዚሁም በምዕራባዊው ሰማይ በሁለተኛው መስኮት ይገባል፤ በዚያችም ቀን ሌሊቲቱ ዐሥራ አንድ ክፍልን ትሆናለች፤ ቀኒቱም ሰባት ክፍልን ትሆናለች። 39ፀሐይም በዚያች ቀን ከዚያች ከሁለተኛዪቱ መስኮት ወጥቶ በምዕራብ በሁለተኛዪቱ መስኮት ይገባል፤ ወደ ምሥራቅም ይመለሳል። 40ፀሐይም በምሥራቅ በአንደኛዪቱ መስኮት ስለ ምልክትWa 41በዚያችም ቀን ሌሊቲቱ ከቀኒቱ ትረዝማለች፤ ሌሊቲቱም የቀኒቱን ዕጥፍ ትሆናለች፤ በጥንቃቄም ቢቈጠር ሌሊቲቱ ዐሥራ ሁለት ክፍል ትሆናለች፤ ቀኒቱም ስድስት ክፍልን ትሆናለች። 42ፀሐይም መስኮቶቹን ጨረሰ፤ ዳግመኛም በእነዚህ መስኮቶቹ ላይ ዙሮ ሠላሳ ቀን በዚያው መስኮት ይገባል፤ በአንጻሩም በምዕራብ ይገባል። 43በዚያችም ቀን ሌሊቲቱ ከርዝመትWa አንድ እጅ ታጥራለች፤ ይኸውም አንድ ክፍል ነው፤ ሌሊቲቱ ዐሥራ አንድ ክፍል ትሆናለች፤ ቀኒቱም ሰባት ክፍል ትሆናለች። 44ፀሐይም ተመልሶ በምሥራቅ ወደሚወጣበት ወደ ሁለተኛው መስኮት ይገባል፤ በዚያም መስኮቱ ተመልሶ ሠላሳ ቀን ይወጣል፤ ይገባልም። 45በዚያችም ቀን ሌሊቲቱ ከርዝመትWa ታጥራለች፤ ሌሊቲቱ ዐሥር ክፍል ትሆናለች፥ ቀኒቱም ስምንት ክፍል ትሆናለች። 46በዚያችም ቀን ፀሐይ ከዚያች ከሁለተኛዪቱ መስኮት ይወጣል፤ በምዕራብም ገብቶ ወደ ምሥራቅ ይመለሳል። 47ፀሐይም በሦስተኛዪቱ መስኮት ስለ ምልክትWa 48በዚያችም ቀን ሌሊቲቱ ታንሳለች፤ ዘጠኝ ክፍልም ትሆናለች፤ ቀኒቱም ዘጠኝ ክፍል ትሆናለች። 49ሌሊቱም ከቀኑ ጋር ይስተካከላል፤ ዓመቱም በጥንቃቄ ቢቈጠር ሦስት መቶ ስድሳ አራት ቀን ይሆናል። 50የቀንና የሌሊት ርዝመት፥ የቀንና የሌሊትም ማጠር በፀሐይ መንገድ ይለያል። 51ስለዚህም መንገዱ ይረዝማል፤ ቀን ከቀን፥ ሌሊትም ከሌሊት ያጥራል። 52የፀሐይ ሥርዐቱ፥ መንገዱም፥ መመላለሻውም ይህ ነው። 53በተመለሰም ጊዜ ስድሳውን ከንትሮስ ሊፈጽም ይመለሳል፤ ተመልሶም ይወጣል፤ ለዘለዓለም የሚኖር ታላቅ ብርሃንም ይህ ነው። 54ጌታ እንዳዘዘም በእርሱ አምሳል የሚጠራ፥ ከምሥራቅ የሚወጣ ታላቅ ብርሃን ይህ ነው። 55እንደዚህም ይወጣል፤ ይገባልም፤ አይጐድልም፤ አያርፍምም፤ ነገር ግን በመዓልትና በሌሊት በሠረገላ ይሮጣል። 56ብርሃኑም ከጨረቃ ይልቅ ሰባት እጅ ያበራል። 57የሁለቱም መጠናቸው እኩል ነው።