1በዚያችም ቀን ቅዱስ ሚካኤል ለቅዱስ ሩፋኤል እንዲህ ብሎ መለሰለት- “የመንፈስ ኀይሉ ነጥቆ ይወስደኛል። 2ለአለቆች ቅጣት ስለ ተሰወረችው ስለ ፍርድ ጭንቀትም ያበሳጨኛል። 3ስትሠራ የኖረችውን፥ እነርሱም በፊትWa የቀለጡባትን ጭንቀት መታገሥ የሚቻለው ማንነው?” 4ዳግመኛም ቅዱስ ሚካኤል ለሩፋኤል እንዲህ ብሎ መለሰለት- “በእርስዋ ላይ ልቡናውን የማያራራ ማን ነው? 5እንደዚህም ካወጧቸው ከእነዚያ በእነርሱ ላይ ከወጣች ከዚች የፍርድ ቃል የተነሣ ኵላሊቱ የማይታወክ ማን ነው? 6በመናፍስት ጌታ ፊት በቆመ ጊዜም እንዲህ ሆነ፤ ቅዱስ ሚካኤል ሩፋኤልን እንዲህ አለው- “የመናፍስት ጌታ ተቈጥትWaቸዋልና በጌታ ዐይን ምሕረት አይደረግላቸውም። 7በጌታ አምሳል ይሠራሉና፥ ስለዚህ ለዘለዓለሙ የተሰወረ ፍርድ ይመጣባቸዋል። 8እነርሱ ብቻ ፍርዳቸውን ለዘለዓለሙ ይቀበላሉ እንጂ መልአክም ቢሆን ሰውም ቢሆን የሌላውን ድርሻ አይቀበልምና።” 9ከዚህም ፍርድ በኋላ ያስደነግጧቸዋል፤ ያሳዝኗቸዋልም። በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ይችን አሳይተዋልና። 10የእነዚያም መላእክት ስማቸው እነሆ፤ ስማቸውም ይህ ነው። 11አለቃቸው ስማዝያ ነው፤ ሁለተኛውም አርስጢኪፋ ነው፤ ሦስተኛውም አርሚን ነው፤ አራተኛውም ኮከብኤል ነው። 12አምስተኛውም ጡርኤል ነው፤ ስድስተኛውም ሩምያል ነው፤ ሰባተኛውም ዳንኤል ነው፤ ስምንተኛውም ምቃኤል ነው፤ ዘጠነኛውም በረቃኤል ነው፤ ዐሥረኛውም አዛዝኤል ነው፤ ዐሥራ አንደኛውም አርማሮስ ነው፤ ዐሥራ ሁለተኛውም በጠርያል ነው። 13ዐሥራ ሦስተኛውም በሰሳኤል ነው፤ ዐሥራ አራተኛውም አናንያል ነው፤ ዐሥራ አምስተኛውም ጡርያል ነው፤ ዐሥራ ስድስተኛውም ሲምሳፓኤል ነው። 14ዐሥራ ሰባተኛውም ይትርኤል ነው፤ ዐሥራ ስምንተኛውም ቱማኤል ነው፤ ዐሥራ ዘጠነኛውም ጥራኤል ነው፤ ሃያኛውም ራሙኤል ነው፤ ሃያ አንደኛውም አዛዝኤል ነው። 15ያለቆቻቸው አለቆችም እኒህ ናቸው። 16የመቶ አለቃቸውና የአምሳ አለቃቸው፥ የዐሥር አለቃቸውም ስማቸው ይህ ነው- የመጀመሪያው ስሙ ይቆን ነው። 17የመላእክትን 18ሁለተኛው ስሙ አስብኤል ነው፤ ይህም ለቅዱሳን መላእክት 19ሦስተኛውም ስሙ ጋድርኤል ነው፤ በመምታት መግደልን ሁሉ ለሰው ልጆች ያስተማረ ይህ ነው። 20ሔዋንንም ያሳታት እርሱ ነው፤ ለሰው ልጆችም የሞት መሣሪያን ጋሻንና ጥሩርን፥ ለግድያም ሰይፍን ያስተማረ እርሱ ነው። 21ለሰው ልጆችም የግድያ መሣሪያዎችን ሁሉ አስተማረ፤ ከዚያች ቀንም ጀምሮ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ በምድር በሚኖሩ ሰዎች ላይ ይህ ሁሉ ከእርሱ ወጣ። 22አራተኛውም ስሙ ፔንሙዕ ነው፤ ለሰው ልጆችም የመረረውንና የጣፈጠውን ያሳየ ይህ ነው። 23የተሰወረ ጥበባቸውን ሁሉ አሳያቸው፤ ለሰዎችም በጥቁር ቀለምና በወረቀት መጽሐፍ መጻፍን አስተማራቸው። 24ስለዚህም ነገር ከጥንት ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እስከዚችም ቀን ድረስ ብዙ ሰዎች ይስታሉ። እንደ መላእክት ጻድቃንና ንጹሓን ሆነው ይኖሩ ዘንድ ነው እንጂ ሰው ለእንደዚህ ያለ ሥራ አልተፈጠረም ነበርና፥ በቀይ ቀለምና በጥቁር ቀለምም ሃይማኖታቸውን ሊያጸኑ ሰው ለእንዲህ ያለ ሥራ አልተወለደም ነበርና። 25ይህን በማወቃቸው ይጠፋሉ እንጂ ሁሉን የሚያጠፋ ሞት ባልዳሰሳቸውም ነበር። 26ስለዚህም ኀይል ይበላኛል። 27አምስተኛውም ስሙ ካሳድያዕ ነው፤ የነፍሳትንና የአጋንንትን ክፉ መማታትን ሁሉ ለሰው ልጆች ያሳየ እርሱ ነው። 28ከማኅፀን ወጥቶ ይወድቅ ዘንድ ፅንስ ማስወረድንና ነፍስ መግደልን የአስተማረ እርሱ ነው። 29በእባብ መነደፍንና በቀትር የሚሆን ምችን ተባዕ የሚባለው የእባብ ልጅ አስተማረ።