ኢያሱና ካሌብ
1የነዌ ልጅ ኢያሱም በሰልፍ ውስጥ ጽኑዕ ነው። ከሙሴም ቀጥሎ ትንቢት ተናገረ፤ 2እጁን በአነሣ ጊዜ፥ 3ከእርሱ አስቀድሞ እንደ እርሱ የሆነ ማንነው? 4ፀሐይ በቃሉ የቆመች አይደለምን? 5በዙሪያው ያሉ ጠላቶቹ በአስጨነቁት ጊዜ 6በተጣሏቸው በአሕዛብም ላይ አዘነበባቸው፤ 7በሙሴም ዘመን ከእነርሱ ጋር ይቅርታን አደረገ፤ 8ከስድስት መቶ ሺህ አርበኞችም የዳኑ እነርሱ ሁለቱ ብቻ ናቸው፤ 9እግዚአብሔርም ለካሌብ ኀይልን ሰጠው፤ 10የእስራኤል ልጆች ሁሉ እግዚአብሔርን መከተል መልካም እንደ ሆነ ያውቁ ዘንድ።