መጽሐፈ ሲራክ 45
ሙሴ
1ሙሴም ስም አጠራሩ የተባረከ ነው፤ 2ከፍ ከፍም አደረገው፤ 3በቃሉም ተአምራትን አደረገ፤ 4ስለ ሃይማኖቱና ስለ የዋህነቱም ቀደሰው፤ 5ቃሉንም አሰማው፤
አሮን
6ከሌዊ ወገን የተወለደ ወንድሙ አሮንም እንደ እርሱ ታላቅ ነው፤ 7የዘለዓለም ሕግንም አጸናለት፤ 8በሁሉም ዘንድ አስመካው፤ 9በዙሪያውም ብዙ ሮማንና የወርቅ ጸናጽል አለ፤ 10የተለየ ሰማያዊ ሐር ያለበት አራት ኅብርን፥ 11የነጭ ሐር የሚሆን ፈትሉ እጥፍ የሆነ፥ 12በማኅተም መልክ አምሳል የተሠራ የወርቅ አክሊልን 13ከእርሱ አስቀድሞ እንደ እርሱ ልብስ ያለ ልብስ አልተሠራም፤ 14ሁልጊዜ በየዕለቱ የጧትና የማታ መሥዋዕት ይሠዉለት ዘንድ፥ 15ሙሴም እጃቸውን ቀባላቸው፤ 16ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ፥ 17ትእዛዛቱን ሰጠው፤ 18ሌሎች ግን ተቃወሙት፤ 19እግዚአብሔርም አያቸው፤ ደስም አላሰኙትም፤ 20ለአሮንም ክብርን ጨመረለት፤ 21ለእርሱና ለልጆቹም የሰጣቸውን የእግዚአብሔርን መሥዋዕት ይበሉ ዘንድ፥ 22የሕዝቡንም ምድር አልተካፈለም፤
ፊንሐስ
23የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስም በክብር ሦስተኛ ነው፤ 24ስለዚህም ለሕዝቡ የቅዱሳንን ሥርዐት ያስተምራቸው ዘንድ፥ 25ከነገደ ይሁዳ ለተወለደ ለዳዊት ልጅም ጌጥ ይሆን ዘንድ፥ 26በልቡናቸውም ጥበብን ያሳድርባቸው ዘንድ፥