1የጠራች ጠፈርን በህዋው ላይ አጸናት፤ 2ብርሃኑን ያሳይ ዘንድ ፀሐይን ያወጣል፤ 3በዋዕዩም ሀገሩን ያቃጥላል፤ 4ዋዕዩንም እሳት እንደሚነድድባት ምድጃ ያደርጋል፤ 5የፈጠረው እግዚአብሔርም ታላቅ ነው፤ 6ጨረቃም ለሁሉ የዘመን መለኪያ ናት፤ 7በጨረቃም የበዓላት ምልክት ይታወቃል፤ 8ጨረቃስ እንደ ስሟ ናት፤ ዕድገትዋም ድንቅ ነው፤ 9የሰማይም ጌጥ የከዋክብት ብርሃን ነው። 10በቅዱሱም ቃል በየሥርዐታቸው ጸንተው ይኖራሉ፤ 11ብርሃኑ ፈጽሞ ያማረ ነውና፥ 12በሰማይ ይከፈላል፤ 13በትእዛዙ በረድ ይዘንባል፤ 14ስለዚህ ነገር መዛግብቱን ይገልጣል፤ 15በገናናነቱም ደመናትን ያጸናቸዋል፤ 16በመጐብኘቱም ተራሮች ይነዋወጣሉ፤ 17የመብረቁም ድምፅ ምድርን ያስፈራታል፤ 18የንጣቱም ውበት ለዐይን ድንቅ ነው፤ 19በረድን እንደ ጨው ያፈስሰዋልና፤ 20የቀዘቀዘው የምሥራቅ ነፋስም ይነፍሳል፤ 21ተራራውን ይበላል፤ 22የሰው ሁሉ ፈውስ ፈጥኖ የሚመጣ ካፊያ ነው፤ 23በእርሱም ምክር ጥልቁ ይደርቃል፤ 24በባሕርም የሚሄዱ ሰዎች መከራዋን ይናገራሉ፥ 25በዚያም ሥራው ፈጽሞ ድንቅ ነው። 26ለበጎ መዓዛም ከእርሱ መሥዋዕት ይሠዋለታል፤ 27ብዙ ነገርን እንናገራለን፤ መፈጸምም አንችልም፤ 28ከፍጥረት ሁሉ እርሱ ይበልጣልና፤ 29እግዚአብሔር የሚያስፈራ ነው፤ 30ጨርሳችሁ ማመስገንን አትጠነቅቁምና፤ 31እርሱን አይቶ የሚነግረን ማን ነው? 32የማይታየው ከዚህ የሚበልጠው ፍጥረቱ ብዙ ነው፤ 33እግዚአብሔር ሁሉን ፈጥሯልና፤