የሰብአዊ ሕይወት ችግር
1የሰው የተፈጥሮው መከራ ታላቅ ነው፤ 2ዕለተ ሞትን ማሰብ በአዳም ልጆች ሁሉ ላይ የምታስደነግጥና ልብንም የምታስፈራ ናት። 3በመንግሥት ዙፋን ከሚቀመጥ ንጉሥ ጀምሮ 4ቀይ ግምጃ ከሚለብስና ዘውድ ከሚቀዳጅ ጀምሮ 5ቍጣና ቅንዓት፥ ንዝንዝና ሁከት፥ ሞትን መፍራትና ክርክር፥ ሐሜትም አለ፤ 6ዕረፍቱ ጥቂት ወይም እንደ ኢምንት ነው፤ 7የሸሸው ሰው ግን ዕለቱን ያመልጣል፤ 8ይህ ሁሉ በሰው ላይ እስከ እንስሳ ድረስ አለ፤ 9ሞትና መታበይ፥ ቸነፈርና ጦርነት፥ ቀጠናና የልብ ቍስል፥ መቅሠፍትም። 10ይህ ሁሉ በኀጢአተኛ ስዎች ላይ ተፈጠረ፤ 11ሁሉ ከምድር ተፈጠረ፤ ሁሉም ወደ ምድር ይመለሳል፤
የክፋት ውጤት
12መማለጃና ዐመፃ ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ 13የዐመፃ ገንዘብ እንደ ፈሳሽ ውኃ ይደርቃል፤ 14እርሱ እጁን ከዘረጋ ደስ ያሰኛል፤ 15የኀጢአተኞች ልጆች ቅርንጫፎቻቸው አይበዙም፤ 16በውኃና በወንዝ ዳር የበቀለ አረምም ከሣሩ ሁሉ ቀድሞ ይነቀላል። 17ጸጋ ግን በበረከት እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፥ 18የሚዘጋጅና የሚሠራ ሰው ሕይወቱ ጣፋጭ ነው፤ 19ልጆችና የሀገር ሕንጻ ስምን ያስጠራሉ፤ 20ወይንና ማሕሌት ልብን ደስ ያሰኛሉ፥ 21በገናና መሰንቆ ሰውነትን ደስ ያሰኙኣታል፤ 22ደም ግባትና ውበት ዐይንን ደስ ያሰኙኣታል። 23ወዳጅና ጓደኛ በዘመናቸው ይጠቅማሉ፤ 24ወንድሞችና ረዳት በመከራ ቀን ይጠቅማሉ፤ 25ወርቅና ብር ሀገርን ያጸናሉ፤ 26ባለጸግነትና ገንዘብ ልቡናን ደስ ያሰኛሉ፤ 27እግዚአብሔርን መፍራት በበረከትዋ እንደ እግዚአብሔር ገነት ናት፤ 28ልጄ ሆይ! በጉልበትህ ሳለህ ልመናን አትውደዳት፤ 29የሌላ ማዕድ ደጅ የሚጠናና ተስፋ የሚያደርግ ሰው፤ 30ለማያፍር ሰው አፍ ልመና ጣፋጭ ነው፤