የምስጋና መዝሙር
12ዳግመኛም አስቤ እናገራለሁ፤ 13የጻድቃን ልጆች ስሙኝ፤ ለምልሙ፤ ታደሱ፤ 14እንደ ሊባኖስ መዓዛ መዓዛችሁ ይጣፍጥ፤ 15ስሙን አግንኑት፤ 16“የእግዚአብሔር ሥራው ገናና ነው። 17“ይህ ለምንድን ነው? ያስ ለምንድን ነው?” ማለት አይገባም፤ 18በትእዛዙም ሁሉ የተወደደ ነው፤ 19የሰው ሁሉ ሥራ በፊቱ ነው፤ 20ዓለም ሳይፈጠር እስከ ዘለዓለም ድረስ ሁሉን ዐወቀ፤ 21ሁሉም ለመፍቅዳቸው ተፈጥሯልና 22በረከቱም እንደ ፈሳሽ ውኃ መላች፤ 23እንደዚሁ ቍጣው አሕዛብን ከፈለቻቸው። 24የጻድቅ መንገዱ የቀና ነው፤ 25በጎ ነገር ከጥንት ጀምሮ ለበጎ ሰዎች ተፈጠረች፤ 26የሰው የመፍቅዱ ሁሉ መጀመሪያ፥ 27ይህ ሁሉ ለጻድቃን ሰዎች በረከታቸው ነው፤ 28ለበቀል የተፈጠረች መንፈስ አለች፤ 29እሳት፥ በረድ፥ ረኃብና ቸነፈር ይህ ሁሉ ለበቀል ተፈጠረ። 30የምድር አራዊት ጥርስ ጊንጥና እፉኝት፥ 31እርሱ ግን በይቅርታው ደስ ያሰኛል፤ 32ስለዚህ ነገር ከጥንት ጀምሮ ሁሉም ተዘጋጀ፤ 33የእግዚአብሔር ሥራው ሁሉ ያማረ ነውና፤ 34“ይህን ክፉ ፈጠርህ፤ ያንም አሳመርህ” የሚለው የለም። 35አሁንም በፍጹም ልቡናችሁ፤ በፍጹምም አንደበታችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤