ባለ መድኀኒትና መድኀኒት
1ባለ መድኀኒትን አክብረው፥ 2ማዳን ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሲሆን፥ 3ሰው ሁሉ ባለ መድኀኒትን በጥበቡ ያከብረዋል፤ 4እግዚአብሔር መድኀኒትን ከምድር ፈጠረ፤ 5ኀይሉን ያውቁ ዘንድ፥ 6በጌትነቱ ይከብሩ ዘንድ፥ 7በመድኀኒቱ ያድናቸዋል፤ 8ያድኑ ዘንድ ከእነርሱ መድኀኒትን ያደርጋሉ፤ 9ልጄ ሆይ፥ በሽታህን ቸል አትበል፤ 10ኀጢአትን ተዋት፤ እጅህን አቅና፤ 11መባእህን አግባ፤ የመታሰቢያውንም የስንዴ ዱቄት ስጥ፤ 12እግዚአብሔር እርሱን ፈጥሮታልና፤ 13በእጃቸው ፈውስ የሚደረግበት ጊዜ አለና። 14ይረዳቸው ዘንድ፥ ዕረፍትንም ይሰጣቸው ዘንድ፥ 15ፈጣሪውን የሚበድል በባለ መድኀኒት እጅ ይወድቃል።
ለሞተ ሰው መታሰቢያ ስለ ማድረግ
16ልጄ ሆይ፥ ለሞተ ሰው አልቅስለት፥ እዘንለትም፤ 17እንደ ልማዱ መራራ ልቅሶ አልቅስለት፤ 18ከዚህ በኋላ ልቅሶህን ተው። 19ኀዘንና ትካዜ ለሞት ያደርሳል፤ 20ኀዘንን ወደ ልቡናህ አታግባ፤ 21ድኅነት እንደሌለባት ዕወቅ፤ ራስህንም ትጎዳለህ፥ 22እኔ የተቀበልሁትን ፍዳ አስተውል፤ 23የሞተ ሰውስ ዐረፈ፤ 24የጸሓፊ ጥበቡ በተሾመበት ወራት ነው፤ 25ዕርፉን የሚያጸና ሰው በምንም አይራቀቅም፥ 26አሳቡ እርሻውን እንዲያርስ ነው፤ 27ሌሊቱ ቀን የሚሆንባቸው ጠራቢና የጠራቢዎች አለቃ፥ 28በወናፍ አጠገብ የሚቀመጥ፥ የብረትንም ሥራ የሚማር አንጥረኛ እንደ እርሱ ነው። 29በሥራው የሚቀመጥ ሸክላ ሠሪም እንደ እርሱ ነው፥ 30በእጁም ጭቃውን መስሎ ይሠራል፤ 31እነዚህ ሁሉ የእጃቸውን ሥራ ተስፋ ያደርጋሉ፤ 32ያለ እነርሱም ሀገር መኖር አትችልም። 33ነገር ግን በሸንጎ ምክርን አያስመክሯቸውም፤ 34ነገርን መስሎ በመናገር አይኖሩም፤ 35ዕውቀት ግን በልቡ ለሚተጋ ሰው ነው።