1ወዳጅ ያበጀ ሰው ሁሉ እኔም ወዳጁ ነኝ ይላል፤ 2በልቡናው ግን እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ኀዘን ይኖራል፤ 3ክፉ ምኞት ሆይ! ከወዴት ተገኘሽ፤ 4በደስታህ ጊዜ የሚቀርብህ ወዳጅ አለ፤ 5በበሽታህ ጊዜ ስለ ሆዱ የሚያዝንልህ ወዳጅ አለ፤ 6በተመቸህ ጊዜ ወዳጅህን አትርሳ፤ 7መካር ሁሉ ምክርን ይመክራል፤ 8ከሚመክርህ ሰው ልቡናህን ጠብቅ፤ 9ገንዘብህን የሚያጠፋብህን ነገር ያመጣብሃል 10ከሚጠባበቅህ ሰው ጋራ አትማከር፤ 11ከሴት ጋር ስለሚያስቀናት ነገር አትናገር፤ 12ሃይማኖት እንዳለው ከምታውቀው፥ እግዚአብሔርንም ከሚፈራ፥ 13እርስዋ ከሁሉ ይልቅ ታማኝህ ናትና፤ 14የሰው ልቡና ከሰባት ጠባቂዎች ይልቅ 15ከዚህ ሁሉ ጋር መንገድህን በእውነት ያቀናልህ ዘንድ፥ 16የመፍቅድ ሁሉ መጀመሪያ ቃል ነው፤ 17የሰው የልቡ ምልክት በአራቱ ወገን ይታያል። 18እነዚህም ኀዘንና ደስታ ሞትና ሕይወት ናቸው። 19ሁሉን የሚማር፥ ብዙም የሚያውቅ ሰው አለ፤ 20በነገር የሚራቀቅ፥ ነገር ግን ራሱን የሚያስጠላ ሰው አለ። 21እግዚአብሔር ሞገስን አይሰጠውምና 22በራሱ የሚራቀቅ፥ 23ብልህ ሰው ወገኖቹን ይመክራቸዋል፤ 24ብልህ ሰው በበረከት ይጠግባል፤ 25የሰው ዘመኑ በቍጥር ነው፤ 26ለወገኖቹ ጥበበኛ የሆነ ሰው ዋጋውን ያገኛል፤ 27ልጄ ሆይ፥ በሕይወት ሳለህ ሰውነትህን ፈትናት፥ 28ሁሉ ለሰውነት የሚገባት አይደለምና፥ 29ለመብል ሁሉ አትሰስት፤ 30ብዙ መብላት ደዌ ይሆናልና፤ 31ስስት የገደላቸው ሰዎች ብዙ ናቸው፥