1ይፈትኑት ዘንድ ነው እንጂ፥ 2ብልህ ሰው መጽሐፍ መስማትን ይወድዳል፤ 3ብልህ ሰው አምኖ በእግዚአብሔር ሕግ ይገዛል፤ 4የምትናገረውን ነገርህን አዘጋጅተህ አድምጥ፤ 5የሰነፍ ሰው ልቡና እንደ ሰረገላ መንኰራኵር ነው፤ 6ጮሌ ፈረስ እንደ በጎ ወዳጅ ነው። 7የዓመቱ ቀን ሁሉ በፀሐይ ብርሃን ጸንቶ ሲኖር፥ 8ቀኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይለያል፤ 9ከቀኑም የቀደሰውና ያከበረው አለ። 10እኛ ሁላችን የአዳም ልጆች ከመሬት ተገኘን፤ 11እግዚአብሔርም በጥበቡ ብዛት ለያቸው፤ 12ከእነርሱም የባረካቸውና ከፍ ከፍ ያደረጋቸው አሉ፤ 13እኛ ሁላችን በእርሱ ዘንድ በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ ጭቃ፥ ነን፤ 14የክፋት ተቃራኒዋ በጎነት ናት፤ 15ከዚህ ሁሉ ጋር የልዑልን ፍጥረቶች ተመልከት፤ 16እኔ ግን ከሁሉ በኋላ ተነሥቼ ይኽን ነገር አሰብሁት፥ 17አቤቱ በስምህ የተጠሩ ወገኖችህን ይቅር በል፤ 18ቅድስት ከተማህን፥ 19ጽዮንንም የቃልህን በረከት ሙላት፤ 20አስቀድሞ ለፈጠርሃቸው ሕግህን ስጣቸው፤ 21ነቢያትህን ያምኗቸው ዘንድ ተስፋ ላደረጉህ ዋጋቸውን ስጣቸው። 22የአሮንንም በረከት በሕዝብህ ላይ አሳድር፤ 23እህል ሁሉ ይበላል፤ ወደ ሆድም ይወርዳል፤ 24የእህልን ጣዕም ሁሉ ጕሮሮ ይለየዋል፥ 25ክፉ ልቡና ኀዘንን ያመጣል፤ 26ወንድ ሁሉ ሚስት ያገባል፤ 27የሴት ውበቷ ፊትን ያበራዋል፤ 28የዋህ ብትሆን፥ ቃሏም ያማረ ቢሆን፤ 29ረዳቱ፥ መደገፊያ ምሰሶውም ናትና፥ 30ቅጥር የሌለው ቤት ገንዘቡ እንዲሠረቅ፥ 31ከከተማ ወደ ከተማ የሚዞር ሌባን የሚዋሰው ማን ነው?