1አለቃም አድርገው ቢሾሙህ ራስህን አታኵራ፤ 2ሥራህን ጨርሰህ ዕረፍ፤ 3ሽማግሌ ሆይ፥ ተናገር፤ ይገባሃልም፥ 4ለመረመረህ ሰው ሁሉ ቃልህን አትናገር፤ 5በወርቅ ጌጥ ክቡር ዕንቍ ደስ እንደሚያሰኝ፥ 6በወርቅ ዝርግፍ ላይ ዕንቍ እንደሚያምር፤ 7ጎልማሳ! ከተፈቀደልህ ተናገር፤ 8አንድ ጊዜ ተናግረህ፥ ወዲያውኑ ነገርህን ጨርስ፤ 9በታላላቆች መካከል አትቀመጥ፤ 10መብረቅ ከነጐድጓድ በፊት እንደሚሮጥ፥ እንዲሁ የሚያፍር ሰው መከበሩ በፊቱ ነው። 11ወደ ቤትህ ገብተህ ሁሉን በጊዜው መጥነህ አድርግ፤ 12የሚገባውንና የሚወደደውንም ሁሉ አድርግ፤ 13ከዚህ ሁሉ ጋራ ፈጣሪህን አመስግነው፤
ሕግን መተርጐም
14እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ለሕጉ ይገዛል፤ 15ሕጉንም የሚፈልገው ከእርሱ ይጠግባል፤ 16እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሰዎች ፍርድን ያገኛሉ፤ 17ኀጢአተኛ ሰው ግን የሚመክሩትን አይሰማም፤ 18ብልህ ሰው ያለ ምክር የሚሠራው ሥራ የለም፤ 19ልጄ ሆይ፥ አንተ ግን ያለ ምክር የምትሠራው ሥራ አይኑር፤ 20በጥፋት ድንጋይ እንዳትሰነካከል፥ 21ጠላትህን በምድረ በዳ አትመነው። 22በፈቃድህ የማይሄድ ልጅህን ስንኳ አትመነው። 23በሠራኸው ሥራ ሁሉ ሰውነትህን ደስ አሰኛት፥ 24ሕጉን የሚጠብቅ ሰው የመጽሓፉን ትእዛዝ ይሰማል፤