ስለ እስራኤል ድኅነት የቀረበ ጸሎት
1የኀይል ሁሉ ፈጣሪ አቤቱ፥ ይቅር በለን፤ ተመለስልንም። 2በአሕዛብ ሁሉ ላይ አንተን መፍራትን አሳድር። 3ልዩ በሆኑ ወገኖችም ላይ እጅህን አንሣ፤ 4እነርሱ እያዩ በእኛ ዘንድ እንደ ተመሰገንህ፥ 5አቤቱ ያለአንተ ሌላ ፈጣሪ የለምና፥ 6ተአምራትህን አሳይ፤ 7በእጅህ ኀይል በቀኝህም ክብር፥ 8ጥፋትን አምጣባቸው፤ 9ዐመፀኛውንም አጥፋው፤ 10ድንቅ ሥራህን ይነግሩ ዘንድ የባሮችህን መሐላ አስብ፤ 11በቍጣና በእሳት ቅሠፋቸው፤ 12ያለ እኛ ሌላ ሰው የለም የሚሉ የጠላቶችን አለቆች ራስ ስበር። 13የያዕቆብን ልጆች ሁሉ ሰብስባቸው።