1ሕጉን የሚጠብቅ ሰው መባ ያገባል። 2ትእዛዙን የሚሰማ ሰውም ለድኅነቱ መሥዋዕትን ይሠዋል። 3ስንዴ የሚያገባ ሰው ዋጋውን ይመልሳል። 4ምጽዋትን የሚመጸውት ሰውም የምስጋና መሥዋዕትን ሠዋ። 5የእግዚአብሔር ፈቃዱ ክፉ እንዳትሠራ ነው፤ 6ወደ እግዚአብሔር ፊት ባዶህን አትግባ። 7ይህን ሁሉ ስለ ትእዛዙ አድርግ። 8የጻድቅ ሰው መሥዋዕት ምሠዊያውን ያለመልመዋል፤ 9የጻድቅ ሰው መሥዋዕት ቅዱስ ነው፤ 10በደስታ ዐይን እግዚአብሔርን አመስግነው፤ 11የሰጠህን ሁሉ ፊትህን ደስ እያለው ስጠው፤ 12እንደ ክብሩ ብዛት መጠን ለእግዚአብሔር መባእህን አግባ፤ 13እግዚአብሔር ዋጋህን ይመልስልሃልና፤ 14አይቀበልልህምና መማለጃን አታግባለት። 15እግዚአብሔር የእውነት ዳኛ ነውና፥ 16ድሃውን ስለ ችግሩ አይለየውም፤ 17የሙት ልጅ ልመናን ቸል አይልም፤ 18እንባንም በፊትዋ ላይ ብታወርድ፥ 19እንደዚሁ ባስለቀሳት ሰው ላይ እንባ ይወርዳል። 20በእውነት የሚያገለግለውን ሰው ይቀበለዋል፤ 21የትሑት ጸሎት ከደመና ታልፋለች፥ 22ለጻድቃን ይፈርድላቸዋል፤ ይበቀልላቸዋልም፤ 23አሕዛብን ይበቀላቸዋል፤ ዐመፀኞችንም ሁሉ ያጠፋቸዋል፤ 24ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ይከፍለዋል። 25ስለ ሰዎችም ሁሉ እንደ ሥራቸውና 26በመከራ ጊዜ የሚገኝ ምሕረት