ስለ ሕልም ከንቱነት
1ሰነፍ ሰው ግን ሐሰትን በከንቱ ተስፋ ያደርጋታል፤ 2ሕልምን የሚያምን ሰው ጥላን እንደሚጨብጥ፤ 3ሕልም ከዚህ ወደዚህ ይሄዳል፤ 4ከርኩስ ምን ንጹሕ ይወጣል? 5ሕልም፥ ጥንቆላና ሟርት ሁሉም ከንቱ ናቸው፤ 6ይቅር ይል ዘንድ ከእግዚአብሔር የተላከ ከአልሆነ፥ 7ሕልም ብዙ ሰዎችን አስትዋቸዋልና፤ 8ያለ ሐሰትስ ከታየ በእውነት ይደርሳል፤ 9የተማረ ሰው ብዙ ምክርን ያውቃል፤ 10ያልተነካ ሰው ግን የሚያውቀው ነገር የለም። 11ብዙ መከራ የተቀበለ ሰው ብዙ ትምህርት ይማራል። 12መከራን በተቀበልሁ ጊዜ ብዙ አየሁ፤ 13ለሞት እስክደርስ ድረስ ሁልጊዜ መከራን ተቀብያለሁና፤ 14እግዚአብሔርን የምትፈራ ነፍስ ትድናለች። 15እርሱን ተስፋ ያደረጉ ሁሉ ይድናሉ። 16እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውን የሚያስፈራው የለም፤ 17እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነፍስ ብፅዕት ናት። 18እርሱ ያድርበታልና፥ የታመነ ወዳጁም ነውና። 19የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ወደ ወዳጆቹ ናቸው፤ ኀይሉ የታመነ ነው፤ ጥግነቱም ጽኑ ነው፤ ቃጠሎውን ያቀዘቅዝልሃል፤ 20ሰውነትህን ያገናታል፤ ዓይኖችህንም ያበራቸዋል፤ 21የበደል መባእ መሥዋዕት ርኩስ ነው፤ 22የኀጢአተኞችም መባእ ተቀባይነት የለውም። 23በመባህ ብዛት ኀጢአትህ የሚሰረይልህ አይደለም። 24በዐመፃ ገንዘብ መባእን የሚያገባ ሰው፤ 25የድሃ ሕይወቱ ምጽዋት መለመን ነው፤ 26ባልን ከሚስቱ የሚያፋታ ሰው፥ 27የምንደኛውን ደመወዝ የቀማ ሰው፥ 28አንዱ ሲሠራ አንዱ ቢያፈርስ፥ 29አንዱ ሲመርቅ ሌላው ቢረግም፥ 30ሬሳ ከዳሰሰ በኋላ እጁን ቢታጠብ፥ 31እንዲሁ ስለ ኀጢአቱ የሚጾም ሰው ዳግመኛ ይበድል ዘንድ ከሄደ፥