ስለ ልጆች
1ልጁን የሚወድ ሰው በፍጻሜው በእርሱ ደስ ይለው ዘንድ፥ 2ልጁን የሚቀጣ ሰው በእርሱ ደስ ይለዋል፤ 3ልጁን ያስተማረ ሰው ጠላቱን ያስቀናል፥ 4ከእርሱ በኋላ እንደ እርሱ ያለ ልጅ ተክትዋልና 5በሕይወቱም ሳለ በልጁ ደስ ይለዋል፤ 6ከእርሱ በኋላ ጠላቶቹን የሚበቀል፥ 7ልጆቹን የሚያባልግ ሰውነቱ ይቈስላል፤ 8ያልተገራ ፈረስ ገርጋሪ ይሆናል፤ 9ልጅህን ካቀማጠልኸው ይበረታታብህ ዘንድ ይመለሳል፤ 10እንዳያሳዝንህም አትሳቅለት፤ 11በወጣትነቱ ጊዜ ልጅህን ስድ አትልቀቀው። 12በአደገ ጊዜ እንዳያምፅብህ 13በእርሱ ጥፋት እንዳታፍር
ስለ ጤንነት
14ሰውነቱ ከታመመና ሆዱ ከታሰረ ባለጸጋ፥ 15ሰውነትህ ጤነኛ ይሁን፤ 16በጤና ከመኖር ባለጸግነት አይመረጥም፤ 17ከመረረ ኑሮና ከቍርጥማት በሽታ ሞት ይሻላል። 18በተዘጋ አፍ የሚቀርብ መብል 19ለጣዖታት መሠዋት ምን ይጠቅማል? 20ጃንደረባ ቆንጆዪቱን ባቀፋት ጊዜ እንደሚያዝን፥ 21ነፍስህን አታሳዝን፤ 22የልቡና ደስታ ለሰው ሕይወቱ ነው፤ 23ኀዘንን ከአንተ ታርቃት ዘንድ ልብህን አጽናናት፤ 24ቅናትና ቍጣ የሕይወት ዘመንን ያሳንሳሉ፤ 25አጫጅን እየተከተለ እንደሚቃርም ሰው፤ 26ጠቢባን ይሆኑ ዘንድ ለሚወዱ ሰዎችም ሁሉ ነው እንጂ፥ 27የሕዝቡ መኳንንት ስሙኝ፥ 28ልጅህንና ሚስትህን፥ ወንድምህንና ወዳጅህን አንተ በሕይወት ሳለህ፥ በገንዘብህ ላይ አታሠልጥናቸው 29አንተ በሕይወት ሳለህ፥ 30አንተ የልጆችህን እጅ ደጅ ከምትጠና፤ 31በምትሠራው ሥራ ሁሉ ብልህ ሁን፤ 32የሕይወት ዘመንህ ሁሉ በአለቀ ጊዜ፤ 33አህያህን ገለባ አብላው፤ ጫነው፤ በአለንጋም ግረፈው፤ 34አገልጋዮችህንም እንዲሠሩ አድርጋቸው፤ ዕረፍትንም ታገኛለህ፤ 35ቀንበር መጫን አንገትን ዝቅ ያደርገዋል፤ 36አገልጋይህን እንዲሠራ አድርገው፥ 37ቦዘኔነት ብዙ ክፋትን ታስተምራለችና። 38የሚችለውን ያህል ሥራውን ስጠው፤ 39አገልጋይ ቢኖርህ እንደ ራስህ ይሁን፤ 40ክፉ ነገር ብታደርግበት ግን ይኰበልልብሃል፤ ያመልጥሃልም፤