መጽሐፈ ሲራክ 29
ስለ ማበደርና መበደር
1ምጽዋትን የሚመጸውት ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ 2በደስታው ጊዜ ከእርሱ ጋር ደስ ይልህ ዘንድ፥ 3ቃልህን ጠብቅ፤ ከእርሱም ጋራ ተማመን፤ 4የብድርን ገንዘብ በምድር ላይ ወድቆ ያገኙት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው፤ 5እስኪበደርህ ድረስ ራስህን ይስምሃል፤ ቃሉንም ያለሰልሳል፤ 6እኩሌታውን ቢከፍልህ በጭንቅ ነው፤ 7ገንዘባቸውን እንዳያጡና እንዳይጣሉ በመፍራትና ጠብን ባለመውደድ ገንዘባቸውን የማያበድሩ ሰዎች ብዙ ናቸው።
ስለ ምጽዋት
8ድሃዉን ግን ታገሠው፤ 9ችግረኛ ነውና በሕግ እንደ ታዘዘው ድኃዉን በምጽዋት ተቀበለው፤ 10ባልንጀራህንና ወዳጅህን ከምታጣ፥ 11ስለ ልዑል ትእዛዝ በወርቅህ አስተዋፅኦ አድርግ፤ 12ምጽዋትን በቤቶችህ አድልባት፤ እርስዋም ትሻላለች፤
ስለ ዋስትና
13ከጦርና ጋሻ ትሻላለች፤ 14ደግ ሰው ጎረቤቱን ይዋሰዋል፤ 15ስለ አንተ ፋንታ ሰውነቱን አሳልፎ ሰጥትዋልና 16ጠብን ለማጥፋት መዋስ ደግ ነገር ነው። 17ኀጢአተኛ ሰው ግን ያዳነውን ሰው ውለታ ይዘነጋል። 18መዋስ ብዙ ደጋግ ሰዎችን አሳዘነ፤ 19ኀጢአተኛ ሰው ግን በመዋስ ይጠፋል፤ 20በተቻለህ መጠን ባልንጀራህን ርዳው፤ 21የሕይወትህ መጀመሪያ እህልና ውኃ፥ ልብስም ነው፤ 22በሌላ ሰው ገንዘብ በባዕድ ቤት ፈጽመህ ደስ ከሚልህ፥ 23ለታናሹም ለታላቁም ሥራህንና ቃልህን አሳምር። 24ካንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት የሚዞር ሰው ኑሮው ክፉ ነው፤ 25ያም ባይሆን ታበላለህ፤ ታጠጣለህም፤ 26በተዘጋጀህ ጊዜ ግን እንዲህ ይሉሃል፥ “እንግዳችን ገብተህ ማዕድን ሥራ፤ ያለህንም አብላን።” 27ብትቸገር ግን፥ “እንግዳችን ውጣ፤ 28ይህ ነገር በብልህ ሰው ዘንድ ጭንቅ ነው፤