መጽሐፈ ሲራክ 22
ሰነፍና ስንፍና
1ሰነፍ ሰው በተቀመጠበት ቦታ እንደ ዋሻ ድንጋይ ነው፤ 2ሰነፍ ሰው በተኛበት ቦታ እንደ ተጣለ ፈርስ ነው። 3ያልተቀጣ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፤ 4ብልህ ሴት ልጅ ባልዋን ትወርሳለች፤ 5አባትዋንም ታሳፍራለች፤ ባሏንም ታሳፍራለች፤ ደፋርም ናት፤
ጥበብና ሞኝነት
6ባገኘበት ቦታ ነገሩን የሚናገር ሰው፥ 7ሰነፍ ሰውን የሚያስተምር ሰው፥ የተሰበረ ገልን እንደሚጠግን ሰው ነው፤ 8ለሰነፍ ሰው የሚነግር በጽኑዕ እንቅልፍ ለተያዘ ሰው እንደሚነግር ነው፤ 9ብርሃኑ አልፏልና ለሞተ ሰው አልቅስለት፤ 10ከሞተ በኋላ አይመለስምና፥ 11ሰዎች ስለ ሞተ ሰው ሰባት ቀን ያለቅሱለታል፤ 12ከሰነፍ ሰው ጋራ ነገርን አታብዛ፤ 13ከእርሱ ራቅ፤ ሰውነትህም ታርፋለች፤ ይቀልሃልም፤ 14ከአረር የሚከብድ ምን አለ? 15ከሰነፍ ሰው ጋራ ከመኖር፥ 16ማገሩ ያማረ፥ በግንብ የታሰረ ቤት በምድር መናወጥ ጊዜ እንደማይፈርስ፥ 17ቅጥሩም ለዘለዓለም አይወድቅም፤ 18በነፋስ ፊት ያለ ገለባም ነፋስ በነፈሰ ጊዜ እንደማይቆም፥
ወዳጅነትን ጠብቆ ማቈየት
19ዐይኑን የሚጠነቍል ሰው እንባውን ያወርዳል፤ 20በወፎች ድንጋይ የወረወረባቸው ሰው ያባርራቸዋል፤ 21በወዳጅህ ላይ ሰይፍን ብትመዝ፥ 22ነገር ግን ብትላገድበት፥ 23አንተም ድሃ ብትሆን በደስታው ጊዜ ከእርሱ ጋር ደስ ይልህ ዘንድ፥ 24የእሳትም የጭሱ ትነት ይቀድማል፤ 25ወዳጄን መሰወር አላፍርም፤ 26ነገር ግን በእርሱ ምክንያት ክፋት ብታገኘኝ፥ 27ለአንደበቴ ጠባቂ ማን ባኖረልኝ?