1ልጄ ሆይ፥ የበደልኸው በደል የሳትኸውም ነገር ቢኖር፥ 2ከክፉ አውሬ እንደሚሸሽ እንዲሁ ከኀጢአት ሽሽ፥ 3ሁለት አፍ እንዳለው የተሳለ ሰይፍ ኀጢአት ሁሉ እንዲሁ ናት፤ 4መመካትና መኵራት፥ ትዕቢትም ባለጸግነትን ያጠፏታል፤ 5ድሃ በሚለምንበት ጊዜ አፉን እስከ ዦሮው ይከፍታል፤ 6ምክርን የሚጠላ ሰው ኀጢአተኞችን ይከተላቸዋል፤ 7ንግግርን የሚችል ሰው ከሩቁ ይታወቃል፤ 8በብድር ገንዘብ ቤቱን የሚሠራ ሰው፥ 9የኀጢአተኞችም አንድነታቸው እንደ ገለባ ክምር ነው፤ 10የኀጢአተኞች መንገድ ጐፃጕፅ ነው፤ 11ልቡናውን ያጸና ሰው የእግዚአብሔርን ሕግ ይጠብቃል። 12ያልተማረ ሰው ጠቢብ አይሆንም፤ 13የብልህ ሰው ዐሳቡ እንደ ክረምት ውኃ ብዙ ነው፤ 14ያላዋቂ ሰው ልብ እንደ ሰባራ ማድጋ ነው፤ 15አስተዋይ ሰው የጥበብን ነገር በሰማ ጊዜ ያደንቃታል፤ 16የአላዋቂ ሰው ነገሩ በራቀ ጎዳና እንዳለ እንደሚከብድ ሸክም ነው፤ 17የብልህ ሰው ነገሩ በጉባኤ ይሰማል፤ 18ጥበብ በአላዋቂዎች ሰዎች ዘንድ እንደ ፈረሰች ቤት ናት። 19ያላዋቂዎች ትምህርት እንደ ታሰረ እግር ነው። 20አላዋቂ ሰው በሳቀ ጊዜ ቃሉን ከፍ ያደርጋል፤ 21ጥበብ በአስተዋይ ሰው ዘንድ እንደ ወርቅ ጌጥ ናት፥ 22ያላዋቂ ሰው እግር ፈጥና ወደ ቤት ትገባለች፤ 23አላዋቂ ሰው በደጃፍ ሆኖ የሰው ቤትን ይመለከታል፤ 24ለሰው በበር ተጠግቶ ማድመጥ አላዋቂነት ነው፤ 25የለፍላፊ ከንፈር የማይመለከተውን ይናገራል፤ 26ያላዋቆች ልባቸው ባፋቸው ነው፤ 27ኀጢአተኛ ሰው ሰይጣንን ቢረግመው ራሱን መርገሙ ነው። 28ሐሜተኛ ሰው ሰውነቱን ያረክሳል፤