1ለበጎ ነገር ሳይሆን የሚገሥጽ ሰው አለ፤ 2ነገር ግን ከመንቀፍ መገሠጽ ይሻላል። 3ስሕተቱን የሚያምን ከጥፋት ይድናል። 4ፍርድን ያደላ ዘንድ የሚወድ ሰው፥ 5እያወቀ ዝም የሚል ሰው አለ፥ 6የሚመልሰውን አያውቅምና ዝም የሚል ሰው አለ፤ 7ብልህ ሰውም ጊዜውን እስኪያገኝ ድረስ ዝም ይላል፤ 8ነገርን የሚያበዛ ሰውን ይቈጡታል፤ 9ችግሩ የሚያዋርደው ሰው አለ፤ 10የማይጠቅምህን የሚሰጥህ ሰው አለ፤ 11እየተቸገረ ራሱን የሚያኰራ አለ፤ 12በጥቂት ብዙ የሚገዛ አለ፤ 13ብልህ ሰው በቃሉ ራሱን ያስወድዳል፤ 14አላዋቂ ሰው ጥቅምና ተወዳጅነት የሌለውን ገንዘብ ይሰጥሃል፤ 15ጥቂት ቢሰጥህ ብዙ እንደ ሰጠህ ይላገድብሃል፤ 16አላዋቂ ሰው ግን “ወዳጅ አልፈልግም ምን ይጠቅመኛል? 17ሁሉም ሁልጊዜ ያሙኛል፤
የማይገባ ንግግር
18በአንደበትህ አድጦህ ከምትወድቅ፥ 19እንዳገኘ የሚናገር ሰው ራሱን ያስነውራል፤ 20በጊዜው አይናገረውምና፥ 21በተቸገረ ጊዜ እግዚአብሔርን ወደ መፍራት የሚመለስ ሰው አለ፤ 22በማፈርም ሰውነቱን የሚያጠፋ አለ፤ 23በማፈር ላይሰጠው ለወዳጁ ተስፋ የሚሰጠው አለ። 24የሐሰተኛ ሰው ውርደቱ ክፉ ነው፤ 25ከሐሰተኛ ሌባ ይሻላል፤ 26ሐሰተኛ ሰው ፈጽሞ ይዋረዳል፥ ያፍራልም። 27በቃሉ ብልህ የሆነ ሰው ነገሩ ይሰማል፤ 28ምድርን የሚያርሳት የእህሉን ክምር ያበዛል፤ 29እጅ መንሻና መማለጃ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ 30የተሰወረ ጥበብ እንደ ተቀበረ ወርቅ ነው፤ 31ጥበቡን ከሚሰውር ብልህ ሰው፤