1ሰካራም ሠራተኛ አይበለጥግም፥ 2መጠጥና ሴት ጠቢባንን ያስትዋቸዋል፥ 3የዚህም ፍጻሜው ትልና ጥፋት ነው። 4ፈጥኖ የሚያምን ልቡናው ቀሊል ነው፥ 5ልቡናውን ደስ የሚያሰኝ ሰው ይደነቃል። 6ብዙ መናገርንም የሚጠላ ኀጢአቱን ያሳንሣል። 7የሰማኸውን ቃል አታውጣ፥ አትድገመውም፥ 8በወዳጅና በጠላት ዘንድ የምትናገረው ነገር አይኑር፥ 9ቢሰማ አይሰውርልህምና፥ 10የሰማኸውን ቃል አታውጣ፥ 11አላዋቂ ሰው የሰማውን ነገር እስከሚያወጣ ድረስ ይቅበዘበዛል፥ 12የተወጋ ሰውም ጦሩን ከላዩ ይነቅል ዘንድ እንደሚቸኩል፥ 13ወዳጅህን አላደረገ እንደ ሆነ 14ወዳጅህን፥ አልተናገረ እንደ ሆነ 15ወዳጅህን በጥላቻ ነገር ተሠርቶበት ይሆናልና ገሥጸው፤ 16በአንደበቱ የማይሳሳት ማን ነው? 17ቍጣ ሳይበዛ ወዳጅህን ገሥጸው፥ 18ጥበብ ሁላ እግዚአብሔርን መፍራት ናትና፥