1ለዘለዓለም ሕያው የሆነ እርሱ ሁሉን በአንድነት ፈጠረ። 2እውነተኛ እግዚአብሔር ብቻ ነው። 3ሥራውን ያውቅ ዘንድ ማንንም አላሰናበተውም፤ 4ከሀሊነቱንስ ማን መርምሮ ያውቃል? 5መጨመርም የለም፤ መቀነስም የለም፤ 6ሰውን በፈጠረው ጊዜ ያንጊዜ ያዝዘዋል፤ 7ሰው ምንድን ነው? ጥቅሙስ ምንድን ነው? 8በጎነቱ ምንድን ነው? ክፋቱስ ምንድን ነው? 9በባሕር ውስጥ እንደ አንዲት የውኃ ጠብታ፥ ከአሸዋውም ሁሉ እንደ አንዲት የአሸዋ ቅንጣት፥ 10ስለዚህ ነገር እግዚአብሔር ይታገሣቸዋል። 11ፍጻሜያቸው ክፉ እንደ ሆነ አይቶ ዐወቃቸው፤ 12ሰው ባልንጀራውን ብቻ ይቅር ይላል፥ 13ይቈጣል፥ ይገርፋል፥ ይቅር ይላል፥
የተወደደ ምጽዋት
14ልጄ ሆይ፥ በደስታህ መካከል ኀዘንን አታስገባ፤ 15ዝናም ዋዕይን የሚያቀዘቅዘው አይደለምን? 16እነሆ እንግዲህ ከመስጠት መልካም ቃል አይሻልምን? 17ንፉግ ልቡናውን ደስ ሳይለው ይሰጣል። 18ሳትናገር ተረዳ፥ ሳትታመምም ዳን። 19ሳይፈረድብህ ራስህን መርምር፤ 20ሳትደክም ራስህን አዋርድ፥ 21ስእለትህን ፈጥነህ ስጥ፤ 22ሳትሳልም አስቀድመህ ስእለትህን አዘጋጅ፤ 23በተቈጣህም ጊዜ የሞትን ቀን ዐስብ፤ 24በጥጋብህ ወራት የረኃብን ወራት ዐስብ። 25ኑሮ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ትለዋወጣለችና፥ 26ብልህ ሰው ግን ፈርቶ በሁሉ ይጠበቃል፤ 27አስተዋይ ሰው ሁሉ ጥበብን ያገኛታል፤ 28ነገር ዐዋቂዎች ራሳቸው በልቡናቸው ይራቀቃሉ፤ 29አትሂድ፥ የኀጢአትንም ፈቃድ አትከተል፤ 30ለሰውነትህ የምትወድደውን ከሰጠኻት፥ 31በተድላ ብዛት ደስ አይበልህ፤ 32እንዳትያዝ አንተ ድሃ ሳለህ፥ በከረጢትህም ምንም ሳይኖርህ አትበደር።