1እግዚአብሔር ሰውን ከምድር ፈጠረው፥ 2ዓመታትንና ቀናትን በቍጥር ሰጣቸው፤ 3ለእየራሳቸው ኀይልን አሳደረባቸው፤ 4ፍጥረቱ ሁሉ እንዲፈሩአቸው አደረገ። 5አውሬዎችንና ወፎችንም እንዲገዟቸው አደረገ። 6ቃልንና አንደበትን፥ ዐይንና ጆሮን፥ 7ጥበብን ማወቅንም አጠገባቸው፤ 8የሥራውን ገናናነትና መፈራቱንም ያሳያቸው ዘንድ፥ 9ቅዱስ ስሙን ያመሰግኑት ዘንድ። 10የሥራውንም ገናናነት ይናገሩ ዘንድ፥ 11ጥበብን ሰጣቸው፤ 12የዘለዓለም መሐላንም ተማማላቸው፤ 13ዐይኖቻቸውም የጌትነቱን ገናናነት አዩ። 14የጌትነቱንም ቃል ጆሮቻቸው ሰሙ፥ 15ከኀጢአት ሁሉ ተጠበቁ አላቸው፤ 16መንገዳቸውም ሁልጊዜ በፊቱ ነው፥ 17ለአሕዛብ ሁሉ ነገሥታትን አነገሠላቸው። 18እስራኤል ግን የእግዚአብሔር ክፍል ሆነ። 19ሥራቸውም ሁሉ በፊቱ እንደ ፀሐይ ነው፤ 20ኀጢአታቸውም ከእርሱ አልተሰወረችም፤ 21የሰው ምጽዋቱ ከእርሱ ጋራ እንደ ማኅተም ነው። 22የሰው ዋጋው እንደ ዐይን ብሌን ትጠበቅለታለች። 23ኋላ ተመልሶ ዋጋቸውን ይሰጣቸዋል፤ 24ነገር ግን ንስሓ የሚገቡበትን መንገድ ሰጣቸው፤