1ጥቅም የሌላቸው ብዙ ልጆችን አትመኝ፤ 2በእነርሱ እግዚአብሔርን መፍራት ከሌለባቸው፥ 3በሕይወታቸውም አትተማመንባቸው፥ 4በአንድ ዐዋቂ ሀገር ትጸናለችና፥ 5ዐይኔ እንዲህ ያለ ብዙ ነገርን አየች። 6በኀጢአተኞች ወገኖች እሳት ትነድዳለች፤ 7በኀይላቸው የታመኑ የቀደሙ አርበኞችም 8ሎጥ ለኖረባቸው፥ ራሳቸውንም ላኮሩ፥ 9ኀጢአተኞች ሕዝቦችን ይቅር አላላቸውም፤ 10እነዚህም የተሰበሰቡ፥ ልቡናቸውንም ያከፉ፥ 11ክሣደ ልቡናውን ያጸና አንድ ሰው ቢኖር 12ቍጣው እንደ ቸርነቱ ብዛት መጠን ነው፥ 13ኀጢአተኛ ሰው ከዳፋ አያመልጥም፤ 14ምጽዋት ሁሉ ይቅርታን ያመጣል፤ 15“ከእግዚአብሔር አመልጣለሁ፤ 16በብዙ አሕዛብም ዘንድ የሚያውቀኝ የለም። 17የሰውነቴስ ቍጥሯ በዓለም ሁሉ ምንድን ነው?” አትበል። 18እነሆ፥ ሰማይ፥ ከሰማያትም በላይ ያለ ሰማይ፥ 19ተራሮችም፥ የምድርም መሠረቶች፥ 20ይህንም ልብ አያስበውም፤ 21ከሥራውም አብዛኛው ስውር ነው፥ 22እውነት ሥራ መሥራትን ማን ያስተምራል? 23አእምሮ የሌለው ሰው እንዲህ ያስባል፤