ከጓደኛ ስለ መጠበቅ
1አደሮ ማር የዳሰሰ ሰው በእርሱ ይያዛል፤ 2የከበደ ሸክምን አንሥተህ በራስህ አትሸከም፥ 3እንደዚሁ ሁሉ ባለ ጸጋ እርሱ ይበድላል፥ እርሱም ይቈጣል፤ 4የምትጠቅመው ነገር ቢኖር ወደ እርሱ ያቀርብሃል፤ 5ገንዘብ ቢኖርህ ከአንተ ጋራ አንድ ይሆናል፥ 6አንተን የሚፈልግበት ግዳጅ ቢኖረው ያባብልሃል፤ 7በመብሉም ይሸነግልሃል፤ አንድ ጊዜ፥ ሁለት ጊዜ፥ ሦስት ጊዜም ያስትሃል፤ 8እንዳያስትህና እንዳያታልልህ ከእንዲህ ያለ ሰው ተጠበቅ፥ 9ባለጸጋ ያዘዘህን ለጊዜው እሽ በለው፥ 10አትራቅ አትሳትም፥ 11ከእርሱ ጋር ነገርን አታብዛ፤ 12መታሰሩና ጥፋቱ አያሳዝነውምና፥ 13ከገዳይህ ጋር ትሄዳለህና ዕወቅ፤ 14ከብት ሁሉ ዘመዱን ይወድዳል፤ 15ፍጥረቱ ሁሉ እንደ እርሱ ካለ ፍጥረት ጋራ አንድ ይሆናል፤ 16ተኵላ ከበግ ጋር በየት ወዳጅ ይሆናል? 17ውሾችን ከጅቦች ጋር ማን ያስማማቸዋል? 18የሜዳ አህዮች የአንበሶች አደን ናቸው፤ 19ትዕቢተኛ ሰው ራሱን የሚያዋርደውን ሰው ይጸየፈዋል፤ 20ባለጸጋ ቢፍገመገም ወዳጆቹ ይደግፉታል፤ 21ባለጸጋ ቢያድጠው ብዙ ሰዎች ያነሡታል፥ 22ባለጸጋ ቢናገር ሁሉ ዝም ይላል፤ 23ኀጢአት ሳትሠራ ባለጸግነት መልካም ነው፤ 24ደስ ቢለው፥ ቢያዝንም 25ደስ ያለው ልቡና ምልክቱ ብሩህ ገጽ ነው፥