1በጎ ሥራ በሠራህ ጊዜ የበጎነትህን ዋጋ ታገኝ ዘንድ፥ 2ለጻድቅ በጎ አድርግ፥ ዋጋህንም ታገኛለህ፤ 3ኀጢአትን በሚሠራና ምጽዋትን በማይመጸውት ዘንድ፥ 4ኀጢአተኛ እንዳይወስድብህ ለጻድቁ ስጥ። 5ለድሃ መልካም አድርግ፥ ለክፉ ግን አትስጥ፤ 6እግዚአብሔር ኀጢአተኞች ሰዎችን ይጠላቸዋልና፤ 7ለኀጢአተኛ ከምትሰጥ ለጻድቅ ስጥ፤ 8በመከራህም ጊዜ ጠላትህ አይሰወርህ። 9ደስታህ ጠላቶችህን ያሳዝናቸዋል፤ 10የልቡናው ክፋት እንደ ብረት ዝገት ነውና፤ 11በተቸገርህም ጊዜ እያመሰገነ ያገለግልሃል፤ 12እንዳይጎዳህ ባጠገብህ አታቁመው፥ በቦታህም አይቀመጥ፤ 13በእባብ ለተነደፈ አስማተኛ፥ 14ከኀጢአተኛም ሰው ጋር የሚሄድ፥ 15ጠላትህ ከአንተ ጋር አንድ ጊዜ ይቆማል፥ 16ጠላትህ በከንፈሩ ቃሉን ያጣፍጥልሃል፥ 17ብትቸገርም ከሁሉ አስቀድሞ በፊትህ ታገኘዋለህ፤ 18በእጁ ያጨበጭባል፤ ራሱንም ይነቀንቃል፤