1ድሃ በጥበቡ ይከብራል፤ 2ስለ መልከ መልካምነቱ ለሰው አታድላ፤ 3ንብ ከወፎች ሁሉ ታንሳለች፤ 4በልብስህ ጌጥ አትታበይ። 5በምድር የወደቁ መኳንንት ብዙ ናቸው፤ 6ፈጽመው የተዋረዱ መኳንንት ብዙ ናቸው፤ 7ሳትመረምር አትንቀፍ፤ 8ሳትሰማ አትመልስ፤ 9ግዳጅህም ባልሆነ ነገር አትጨነቅ፤ 10ልጄ ሆይ፥ ሥራህን አታብዛ፤ ብታበዛ ትከብር ዘንድ አያሠለጥንህምና፤ 11የሚቸኩልና የሚሠራ፥ የሚደክምም አለ፤ 12ደክሞ ሳለም የማይለምን፥ ምንም ማድረግ ሳይችል የሚገዛ አለ፤ 13እግዚአብሔር ግን በመልካም ዐይን ቢያየው ከችግሩ ያነሣዋል። 14መልካምና ክፉ፥ ሕይወትና ሞት፤ 15ጥበብ፥ ማስተዋልና ሕግን ማወቅ፥ 16ስሕተትና ጨለማ ከመወለዳቸው ጀምሮ ከኃጥኣን ጋር ኖረዋል። 17የእግዚአብሔር ጸጋው ጻድቃንን ትጠብቃቸዋለች፤ 18እየነፈገ በንፍገቱ ብዛት የሚከብር ሰው አለ። 19ያርፍ ዘንድ ተስፋ ባደረገ ጊዜ፥ 20በቃል ኪዳንህ ቁም፤ በእርሱም ተማር፤ 21የኀጢአተኞች ሥራቸው አያስጐምጅህ፥ 22የእግዚአብሔር በረከት ለጻድቃን ዋጋቸው ናት፥ 23“የአገልግሎቴ ትርፍ ምንድን ነው? 24“እንግዲህስ በቃኝ፥ 25በመልካም ቀን ጊዜ ክፉ ይረሳል፤ 26የሞት ቀን በእግዚአብሔር ዘንድ ቀሊል ነው፤ 27በክፉ ቀን ጥጋብ ያቀናጣል፤ 28ፍጻሜውን ሳታይ ሰውን ብፁዕ አትበለው፥