1“እናንተም ነገሥታትና መኳንንት፥ ቃሌን ስሙ፤ ትእዛዜንም ጠብቁ ይላል ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር። የጠበቅኋቸውና ያዳንኋቸው፥ ከወላጆቻቸው ጀምሮ ያሳደግኋቸው፥ በሚፈልጉት ሁሉ የመገብኋቸው፥ 2ወደ ምድርም አዝመራ ያገባኋቸው፥ እንደሚገባም የምድርን በረከት የመገብኋቸው፥ ያልተከሉትን የወይኑን ተክልና የዘይቱን ፍሬ፥ ያልቈፈሩትን የጠራ የውኃ ጕድጓድ፥ 3የማሩን ወለላ፥ የበጊቱንም ወተት፥ ከስንዴው ፍትግ ጋር የጌጡን ልብስና ለእነርሱ የሚያስፈልገውን ሁሉ የሰጠኋቸው፥ አምላካቸው እግዚአብሔር ስሆን፥ እንደ አሳዘኑኝና ሌሎች አማልክትን እንደ አመለኩ እንደ እስራኤል ልጆች አታሳዝኑኝ። 4ከለመኑኝም ያልሰጠኋቸው አልነበረም።