1ድሆች ግን ዳግመኛ በመኝታቸው ያስባሉ፤ ባለጠጎች ካልተቀበሏቸውም ልምላሜ እንደሌለው እንደ ደረቅ እንጨት ይሆናሉ፤ ርጥበትም ከሌለ ሥር አይለመልምም፤ ሥርም ከሌለ ቅጠሉ አይለመልምም። 2ቅጠል ለፍሬ ጌጥ ያገለግላልና ቅጠሉ ካልለመለመ ፍሬ አያፈራም፤ የሰው ራሱ የጽድቅ ፍሬ ነውና ፍሬ የሌለው በጎ ሥራ የለውም። 3ጽድቅን ቢሠራ ቅንነትን ያፈራል፤ እግዚአብሔርም እውነትንና ቅንነትን በሚሠራ ሰው ደስ ይለዋል። 4ለሚጸልይም ጸሎቱንና የአንደበቱን ዋጋ ይሰጠዋል፤ ጻድቁንም ስለ ሠራው ጽድቅ አይበድለውም። 5እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ ጽድቅንም ይወድዳልና ኃጥኡን ስለ ሠራው ክፉ ሥራ ያለ ንስሓ አያጸድቀውም፤ የሰውም ሁሉ ነፍስ በእጁ ተይዟልና፥ ሰማይንና ምድርንም የሚገዛ ነውና በፍርድ ለባለጠጋና ለድሃ ፊት አያዳላም።