ሃሌ ሉያ።
1እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘለዓለም ናትና 2ቸር እንደ ኾነ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ኾነች የእስራኤል ቤት አኹን ይንገሩ 3ቸር እንደ ኾነ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ኾነች የአሮን ቤት አኹን ይንገሩ 4ቸር እንደ ኾነ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ኾነች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ዅሉ አኹን ይንገሩ 5በተጨነቅኹ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራኹት ሰማኝ አሰፋልኝም 6እግዚአብሔር ረዳቴ ነው አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል 7እግዚአብሔር ረዳቴ ነው እኔም በጠላቶቼ ላይ አያለኹ 8በሰው ከመታመን ይልቅ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል 9በገዢዎች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረግ ይሻላል 10አሕዛብ ዅሉ ከበቡኝ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍዃቸው 11መክበቡንስ ከበቡኝ በእግዚአብሔርም ስም አሸነፍዃቸው 12ንብ ማርን እንዲከብ፟ ከበቡኝ እሳትም በሾኽ ውስጥ እንዲነድ፟ ነደዱ በእግዚአብሔርም ስም አሸነ ፍዃቸው 13ገፋኸኝ ለመውደቅም ተንገዳገድኹ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ 14ኀይሌም ዝማሬዬም እግዚአብሔር ነው ርሱም መድኀኒት ኾነልኝ 15የእልልታና የመድኀኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች 16የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኀይልን አደረገች 17አልሞትም በሕይወት እኖራለኹ እንጂ የእግዚአብሔርንም ሥራ እናገራለኹ 18መገሠጽስ እግዚአብሔር ገሠጸኝ ለሞት ግን አልሰጠኝም 19የጽድቅን ደጆች ክፈቱልኝ ወደ እነርሱ ገብቼ እግዚአብሔርን አመሰግናለኹ 20ይህች የእግዚአብሔር ደጅ ናት ወደ ርሷ ጻድቃን ይገባሉ 21ሰምተኸኛልና መድኀኒትም ኾነኸኛልና አመሰግንኻለኹ 22ግንበኛዎች የናቁት ድንጋይ ርሱ የማእዘን ራስ ኾነ 23ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ ኾነች ለዐይናችንም ድንቅ ናት 24እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት ሐሤትን እናድርግ በርሷም ደስ ይበለን 25አቤቱ እባክኽ አኹን አድን አቤቱ እባክኽ አኹን አቅና 26በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ 27እግዚአብሔር አምላክ ነው ለእኛም በራልን እስከመሠዊያው ቀንዶች ድረስ የበዓሉን መሥዋዕት በገመ ድ እሰሩት 28አንተ አምላኬ ነኽ አመሰግንኽማለኹ አንተ አምላኬ ነኽ ከፍ ከፍ አደርግኻለኹ ሰምተኸኛልና መድኀ ኒትም ኾነኸኛልና አመሰግንኻለኹ 29እግዚአብሔርን አመስግኑ ቸር ነውና ምሕረቱ ለዘለዓለም ናትና