የዳዊት መዝሙር።
1እግዚአብሔር የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና ወደድኹት 2ዦሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና በዘመኔ ዅሉ እጠራዋለኹ 3የሞት ጣር ያዘኝ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ ጭንቀትንና መከራን አገኘኹ 4የእግዚአብሔርንም ስም ጠራኹ፦አቤቱ ነፍሴን አድናት 5እግዚአብሔር መሓሪና ጻድቅ ነው አምላካችንም ይቅር ባይ ነው 6እግዚአብሔር ሕፃናትን ይጠብቃል ተቸገርኹ ርሱም አዳነኝ 7ነፍሴ ሆይ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ እግዚአብሔር መልካም አድርጎልሻልና 8ነፍሴን ከሞት ዐይኔንም ከእንባ እግሬንም ከመሰናከል አድኗልና 9በሕያዋን አገር በእግዚአብሔር ፊት እኼዳለኹ 10አመንኹ ስለዚህም ተናገርኹ እኔም እጅግ ተቸገርኹ 11እኔም ከድንጋጤዬ የተነሣ፦ሰው ዅሉ ሐሰተኛ ነው አልኹ 12ስላደረገልኝ ዅሉ ለእግዚአብሔር ምንን እመልሳለኹ 13የመድኀኒትን ጽዋ እቀበላለኹ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለኹ 14በሕዝቡ ዅሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለኹ 15የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው 16አቤቱ እኔ ባሪያኽ ነኝ ባሪያኽ ነኝ የሴት ባሪያኽም ልጅ ነኝ ሰንሰለቴን ሰበርኽ 17ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለኹ የእግዚአብሔርንም ስም እጠራለኹ 18በሕዝቡ ዅሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለኹ 19በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ኢየሩሳሌም ሆይ በመካከልሽም ሃሌ ሉያ