የዳዊት መዝሙር።
1አቤቱ ምሕረትንና ፍርድን እቀኝልኻለኹ 2እዘምራለኹ ንጹሕ መንገዱንም አስተውላለኹ ወደ እኔ መቼ ትመጣለኽ በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እ ኼዳለኹ 3በዐይኔ ፊት ክፉን ነገር አላኖርኹም ሕግ ተላላፊዎችን ጠላኹ 4ጠማማ ልብም አልተጠጋኝም ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅኹም 5ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን ርሱን አሳደድኹ በዐይኑ ትዕቢተኛ የኾነውና ልቡ የሚሣሣው ከእኔ ጋ ራ አይተባበርም 6ከእኔ ጋራ ይኖሩ ዘንድ ዐይኖቼ በምድር ምእመናን ላይ ናቸው በቀና መንገድ የሚኼድ ርሱ ያገለግለ ኛል 7ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም ዐመፅን የሚናገር በዐይኔ ፊት አይቀናም 8ዐመፃ የሚያደርጉትን ዅሉ ከእግዚአብሔር ከተማ አጠፋቸው ዘንድ የምድርን ኀጢአተኛዎች ዅሉ በማለዳ እገድላቸዋለኹ