1ልጄ ሆይ፥ በክፉ ሰዎች አትቅና፥ 2ልባቸው ሐሰትን ይማራልና። 3ቤት በጥበብ ይሠራል፥ 4በዕውቀት ከከበረውና ካማረው ሀብት ሁሉ 5ጠቢብ ሰው ከብርቱ ይሻላል፥ 6በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ 7ጥበብና መልካም ዕውቀት በብልሆች በር ትገኛለች፤ 8ነገር ግን በአንድነት ያስባሉ፥ 9ሰነፍ በኀጢአት ይሞታል፤ 10በመከራ ቀንና በክፉ ቀን 11ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤ 12እነሆ፥ ይህን አላውቅም ብትል፥ 13ልጄ ሆይ፥ ማር ብላ፥ 14እንዲሁም ጥበብን በሰውነትህ ተማር፥ 15ኃጥኣንን ወደ ጻድቃን ቦታ አትውሰድ፤ 16ጻድቅ ሰባት ጊዜ ይወድቃል፥ ሰባት ጊዜም ይነሣል። 17ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ 18እግዚአብሔር ያያልና፥ ደስም አያሰኘውምና፥ 19ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች ደስ አይበልህ፥ 20ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና 21ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔርንና ንጉሥን ፍራ፥ 22እነርሱ ኀጢአተኞችን ድንገት ይበቀሏቸዋልና፤ 23የነገሩትን የሚጠብቅ ልጅ ከጥፋት የራቀ ነው፥ 24ከንጉሥ አንደበት ምንም ሐሰት ይነገራል አይባልም፥ 25የንጉሥ ቃል ሰይፍ ናት፥ 26ሰይፈ መዓቱ ብትሳል ግን ከዘሮቹ ጋር ሰውን ታጠፋለች፤ 27በአሞሮች ጫጩት የማይበላ እስኪሆን ድረስ፥ 28ልጄ ሆይ፥ ነገሬን ፍራ፥ ተቀበለው፥ ንስሓም ግባ፤ 29እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ሰነፍ ነኝና፥ 30እግዚአብሔር ጥበብን አስተማረኝ፥ 31ወደ ሰማይ የወጣ፥ የወረደስ ማን ነው? 32የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጋለ ነው፤ 33እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን 34ሁለትን ነገር ከአንተ እለምናለሁ፥ 35ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ 36እጅግ ጠግቤ ሐሰተኛ እንዳልሆን፦ 37አገልጋይን በጌታው እጅ አሳልፈህ አትስጥ 38ክፉ ልጅ አባቱን ይረግማል፥ 39ክፉ ልጅ የራሱን ጽድቅ ይፈርዳል 40ክፉ ትውልድ ትዕቢተኛ ዐይን አለው፥ 41ድሆችን ከምድር ላይ ችግረኞችንም ከሰው መካከል ያጠፋና ይጨርስ ዘንድ፥ 42በፍርድ ጊዜ የሰውን ፊት ማፈር መልካም እንዳይደለ ታውቁ ዘንድ 43ኃጥኡን፦ “ጻድቅ ነህ” የሚለውን 44የሚዘልፉት ግን መታየትን ያሳምራሉ፥ 45በቀና ነገር የሚመልስ ከንፈር ይሳማል። 46ለመንገድህ ሥራህን አሰናዳ፥ 47በባልንጀራህ ላይ በሐሰት ምስክር አትሁን፥ 48እንዳደረገብኝ እንዲሁ አደርግበታለሁ፥ 49በሰነፍ ሰው እርሻ አለፍሁ። 50እነሆም፥ በላዩ እሾህ በቅሎበታል፥ 51እኔ ንስሓ ከገባሁ በኋላ 52ጥቂት ትተኛለህ፥ ጥቂትም ታንቀላፋለህ፥ 53እንግዲህ ይህን ብታደርግ ድህነት እየቀደመች፥ 54ለአልቅት ሦስት የሚዋደዱ ሴቶች ልጆች አሏት። 55እነርሱም ሲኦልና የሴት ፍቅር፥ 56በአባቱ የሚሥቅ፥ 57ላውቃቸው የማልችል ሦስት ናቸው፥ 58እነርሱም የሚበርር ንስር ዱካ፥ 59ሠርታ የምትታጠብ፦ 60በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ 61ባሪያ በነገሠ ጊዜ፥ ሰነፍም እንጀራን በጠገበ ጊዜ፥ 62የተጠላች ሴት ቸር ባል ባገኘች ጊዜ፥ 63በምድር ላይ አራት ጥቃቅን ፍጥረቶች አሉ፤ 64ገብረ ጕንዳን ኀይል የሌላቸው ናቸው፥ 65ሽኮኮዎች ያልበረቱ ሕዝቦች ናቸው፥ 66አንበጣ ያለ መንግሥት ነው፥ 67እንሽላሊት በእጅ የሚሄድ ደካማ ሲሆን፥ 68መልካም አራማመድን የሚራመዱ ሦስት ፍጥረቶች አሉ፥ 69የአንበሳ ደቦል ከእንስሳ ሁሉ የሚበረታ፥ 70ክንፉን እያማታ በእንስቶች ዶሮዎች መካከል የሚሄድ አውራ ዶሮ፤ 71ራስህን ለቦዘኔነት ብትሰጥ፥ 72ወተትን እለብ ቅቤ ይሆንልሃል፥ 73የእኔ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ተነገረ። 74ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል ምን እንደሆነ ዐውቀህ ተጠበቅ። 75ኋላ እንዳትጸጸት ገንዘብህን፥ ልብህንና ጕልበትህን፥ 76ከምክር ጋር ሁሉን አድርግ፥ 77ወይንን በመጠጣት ጥበብን እንዳይዘነጓት 78ለኀዘንተኞች ወይንን ስጧቸው፥ 79ኀዘናቸውን ይረሱ ዘንድ፥ 80አፍህን በእግዚአብሔር ቃል ክፈት፥ 81አፍህን ክፈት፥ በእውነትም ፍረድ፤