ኢየሩሳሌም ከውድቀት በኋላ
1አሌፍ። ወርቁ እንዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እንዴት ተለወጠ! 2ቤት። ጥሩ ወርቅ የሚመስሉ የከበሩ የጽዮን ልጆች፥ 3ጋሜል። አራዊት እንኳ ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ፤ 4ዳሌጥ። ጡት የሚጠባው የሕፃን ምላስ ከጥም የተነሣ ወደ ትናጋው ተጣበቀ፤ 5ሄ። የጣፈጠ ነገር ይበሉ የነበሩ በመንገድ ጠፉ፤ 6ዋው። የማንም እጅ ሳይወድቅባት ድንገት ከተገለበጠች፥ 7ዛይ። ቅዱሳኖችዋ ከበረድ ይልቅ ነጡ፤ ከወተትም ይልቅ ነጡ፤ 8ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ 9ጤት። በሰይፍ የሞቱት በራብ ከሞቱት ይሻላሉ፤ 10ዮድ። የርኅሩኆች ሴቶች እጆች ልጆቻቸውን ቀቅለዋል፤ 11ካፍ። እግዚአብሔር መዓቱን ፈጽሞአል፤ ጽኑ ቍጣውንም አፍስሶአል፤ 12ላሜድ። የምድር ነገሥታት፥ በዓለምም የሚኖሩ ሁሉ፥ 13ሜም። የጻድቃንን ደም በውስጥዋ ስላፈሰሱ፥ 14ኖን። እነርሱ ታውረው በመንገድ ላይ ተቅበዘበዙ፤ 15ሳምኬት። እናንተ ከርኩሳን ራቁ፥ አስተምሩአቸው፤ ራቁ፥ ራቁ በሉአቸው፤ አትንኩአቸውም። 16ዔ። የእግዚአብሔር ፊት ክፍላቸው ነበረ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከታቸውም፤ 17ፌ። በማያድን ወገን እያመንን ረዳታችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ 18ጻዴ። ልጆቻችንን ወደ አደባባያችን እንዳይወጡ ከለከልን፤ 19ቆፍ። አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስር ይልቅ ፈጣኖች ሆኑ፤ 20ሬስ። ስለ እርሱ፥ “በአሕዛብ ውስጥ በጥላው በሕይወት እንኖራለን” ያልነው፥ 21ሣን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሤትም አድርጊ፤ 22ታው። የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፥ በደልሽ ተፈጸመ፤ ከእንግዲህ ወዲህ አያስማርክሽም።