1“እግዚአብሔር ዘመኖችን ለምን ረሳቸው? 2ኃጥኣን የድንበሩን ምልክት አለፉ፤ 3የድሃአደጎቹን አህያ ይነዳሉ 4ደካሞችን ከእውነት መንገድ ያወጣሉ፤ 5እነሆ፥ በምድረ በዳ እንዳሉ እንደ ሜዳ አህዮች ሆኑ። 6“የራሳቸው ያልሆነውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭዳሉ። 7ብዙዎችን የተራቈቱትንም ያለ ልብስ ያሳድሩአቸዋል። 8በካፊያና ከተራሮች በሚወርድ ጠል ይረጥባሉ፤ 9ድሃአደጉን ልጅ ከጡቱ ይነጥላሉ፤ 10ችግረኞችን በደሉአቸው፥ ጣሉአቸውም፤ 11በጠባብ ቦታ በዐመፅ ይሸምቃሉ፥ 12ድሆችን ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው አባረሩአቸው 13“እግዚአብሔር ግን እነዚህን ለምን አልገሠጻቸውም? 14ሥራቸውንም ዐውቆ ለጨለማ ዳረጋቸው። 15የአመንዝራም ዐይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል፦ 16በጨለማ ቤቶችን ይነድላል፤ 17የጥዋት ብርሃን ለእነርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ 18እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያልፋል፤ 19ተክላቸው በምድር ላይ ሲደርቅ ያያሉ። 20ከዚህም በኋላ ኀጢአቱን ያስባል። 21ለማትወልደው ለመካኒቱ በጎነትን አላደረገላትም፤ 22ነገር ግን ረዳት የሌላቸውን በቍጣው አጠፋቸው። 23በታመመም ጊዜ መዳንን ተስፋ አያደርግም። 24ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። 25እንዲህስ ባይሆን ሐሰተኛ ነህ የሚለኝ፥