ኦሪት ዘዳግም 32
1እንዲህም አለ፦ 2ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ 3የእግዚአብሔርን ስም እጠራለሁና፤ 4እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ 5እነርሱ በደሉ፤ ልጆቹም አይደሉም፤ 6ደንቆሮ፥ ብልሃተኛም ያልሆንህ ሕዝብ ሆይ፥ 7የዱሮውን ዘመን አስብ፤ 8ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ 9ሕዝቡ ያዕቆብም የእግዚአብሔር ዕድል ፋንታ ሆነ፤ 10በምድረ በዳ አጠገባቸው፤ 11ንስር ጫጩቶቹን በክንፎቹ በታች እንደሚሰበስብ፥ 12እግዚአብሔር ብቻውን መራቸው፤ 13በምድር ኀይል ላይ አወጣቸው፤ 14በላሙ ቅቤ፥ በበጉም ወተት፥ 15ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ 16በዚህ በልዩ ጣዖት አነሣሡኝ፤ 17ለእግዚአብሔር ያይደለ ለአጋንንት፥ 18የወለደህን እግዚአብሔርን ተውህ፤ 19እግዚአብሔርም አይቶ ቀና፤ 20እርሱም አለ፦ ፊቴን ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ 21አምላክ ባልሆነው አስቀኑኝ፤ 22እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ 23ለመከራ እሰበስባቸዋለሁ፤ 24በራብ ያልቃሉ፤ 25ጐልማሳውን ከድንግል፥ ሕፃኑንም ከሽማግሌ ጋር፥ 26እበትናቸዋለሁ አልሁ፤ 27ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ 28ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፤ 29ይህንም ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፤ 30አንዱ ሽሁን እንዴት ያሳድዳቸዋል? 31አምላካችን እንደ አምላኮቻቸው አይደለምና፤ 32ወይናቸው ከሰዶም ወይን፥ 33የወይን ጠጃቸው የእባብ መርዝ፥ 34በእኔ ዘንድ ያለው ትእዛዝ ይህ አይደለምን? 35በፍርድ ቀን እበቀላቸዋለሁ፤ 36እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ 37እግዚአብሔርም አለ፦ ትታመኑባቸው የነበሩት አማልክት የት አሉ? 38የመሥዋዕታቸውን ስብ የምትበሉላቸው፥ 39እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ 40እጄን ወደ ሰማይ እዘረጋለሁና፥ 41ሰይፌን እንደ መብረቅ እስላታለሁ፤ 42ከተወጉት፥ ከተማረኩትም ደም፥ 43ሰማያት ሁሉ በአንድነት ደስ ይላቸዋል፤ 44ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
የሙሴ መጨረሻ ምክር
45ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእስራኤል ሁሉ ተናግሮ ፈጸመ። 46እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠብቁና ያደርጉ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዝዙበት ዛሬ የምመሰክርላችሁን ቃል ሁሉ በልባችሁ አኑሩት። 47ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ዘመናችሁ ይረዝማል።”
የሙሴ ሞት መነገሩ
48በዚያም ቀን እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 49“በኢያሪኮ አንጻር በሞዓብ ምድር በዓባሪም ተራራ ውስጥ ወዳለው ወደ ናባው ተራራ ውጣ፤ ለእስራኤልም ልጆች ርስት አድርጌ የምሰጣቸውን የከነዓንን ምድር እያት፤ 50ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ እንደ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም እንደ ተጨመረ፥ በወጣህበት ተራራ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተጨመር፤ 51በእስራኤል ልጆች መካከል በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ባለው በክርክር ውኃ ለቃሌ አልታዘዛችሁምና፥ በእስራኤልም ልጆች መካከል አልቀደሳችሁኝምና፥ 52ምድሪቱን ፊት ለፊት ታያለህ እንጂ ወደዚያች ምድር አትገባም።”