ሩፋኤል የአደራውን ገንዘብ እንደ ተቀበለ
1ጦብያም ሩፋኤልን ጠርቶ እንዲህ አለው፦ 2“አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ፥ ሁለት ብላቴኖችንና ግመሎችን ይዘህ የሜዶን ክፍል ወደምትሆን ወደ ራጊስ ወደ ገባኤል ቤት ሂድ፤ የብሩንም መክሊት አምጣ። እርሱንም ወደ ሰርጉ በዓል ጥራው። 3የሰርጉ በዓል ሳያልቅ እንዳልወጣ ራጉኤል አምሎኛልና። 4አባቴ ግን ቀኑን ይቈጥራል፤ ብዘገይም ፈጽሞ ያዝናል።” 5ሩፋኤልም ሄደ፤ በገባኤልም ቤት አደረ፤ ደብዳቤውንም ሰጠው፤ እነዚያንም ከረጢቶች እንደታተሙ አምጥቶ ለሩፋኤል ሰጠው። 6በጧትም በአንድነት ገሥግሠው ሄዱ፤ ወደ ሰርጉም ደረሱ፤ ጦብያም ያን ብር ባመጣለት ጊዜ ሩፋኤልን መረቀው።