መጽሐፈ ሲራክ 6
1ጠላት ከምትሆን ወዳጅ ሁን፤ 2ከልቡናህ ባነቃኸውም ምክር ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፤ 3ቅጠልህን ይበላብሃል፥ ፍሬህንም ታጣለህ፤ 4ክፉ ሰውነት ገንዘብ ያደረጋትን ሰው ታጠፋዋለች፤
እውነተኛና እውነተኛ ያልሆነ ጓደኝነት
5ልዝብ አንደበት ወንድማማችነትን ያበዛል፤ 6ብዙ ሰዎች ወዳጆች ይሁኑህ፤ 7ወዳጅ ብታበጅ በችግርህ ወራት ወዳጅ አብጅ። 8ለጥቂት ቀን የሚሆን ወረተኛ ወዳጅ አለና፤ 9ጠላት የሚሆንህና፥ የሚሰድብህ፥ 10ስለ ማዕድህም የሚወድህ ወዳጅ አለ፤ 11ባለጸጋ በሆንህ ጊዜ እንዳንተ ይሆናል፤ 12ብትቸገር ግን እርሱ ባላጋራህ ይሆናል፤ 13ከጠላቶችህ ራቅ፥ 14የታመነ ወዳጅ እንደ ጸና አላባሽ አግሬ ጋሻ ነው፤ 15ለታመነ ወዳጅ ለውጥ የለውም፤ 16የታመነ ወዳጅ የሕይወት መድኀኒት ነው፤ 17እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ወዳጅነቱን ያጸናል፤
የጥበብ በረከት
18ልጄ ሆይ፥ በሕፃንነትህ ጥበብን ምረጣት፤ 19እንደሚያርስና እንደሚዘራ ሰው ወደ እርስዋ ሂድ፤ 20በሰነፎች ዘንድ ፈጽማ ጐፃጕፅ ናት፤ 21የፈተና ድንጋይ አንሥተው በተሸከሙት ጊዜ እንዲከብድ፥ 22ጥበብስ እንደ ስሟ ናት፤ 23ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ በምክሬም ጽና፤ 24እግሮችህን ወደ ቀምበርዋ አግባ፤ 25ጫንቃህን ዝቅ አድርገህ ተሸከማት፤ 26በፍጹም ነፍስህ ወደ እርሷ ተሰማራ፥ 27ፍለጋዋን ተከተል፥ ፈልጋት፤ ታገኛታለህም። 28በፍጻሜህም ዕረፍትን ታገኛለህ፤ 29እግር ብረትዋም እንደ ጽኑ ጋሻ ይሆንልሃል፤ 30የዘለዓለም ወርቅ በእርሷ ዘንድ አለና፤ 31እንደ ክብር ልብስ ትለብሳታለህ፥ 32ልጄ ሆይ፥ ብልህ ትሆን ዘንድ ብትወድድ፥ 33ትሰማ ዘንድ ብትወድም ታገሥ፤ 34በብዙ ሽማግሌዎች ዘንድ ቁም፤ 35የመጽሐፉን ነገር ሁሉ ፈጥነህ ስማ፤ 36ብልህ ሰው ብታይ ፈጥነህ ወደ እርሱ ሂድ፤ 37የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ዐስብ፤