የሲራክ ልጅ የኢያሱ ጸሎት
1አቤቱ ንጉሥ ሆይ! እገዛልሃለሁ፤ 2ረድተኸኛልና፥ ሰውረኸኝማልና፥ 3እንደ ቸርነትህ ብዛት መጠን፥ ስለ ስምህም አዳንኸኝ፥ 4ቋያ እንደ ከበበው፥ 5ከታችም ከመቃብር ሆድ፥ 6ወደ ንጉሥ በሚያጣላ ዐመፀኛ አንደበት፥ ሰውነቴ ወደ ሞት ደረሰች፤ 7በዙሪያዬም ከበቡኝ፤ የሚረዳኝም አጣሁ፤ 8አቤቱ ይቅርታህን ዐሰብሁ፥ 9ልመናዬንም ከምድር ወደ ላይ ከፍ ከፍ አደረግሁ፤ 10አባቴና ጌታዬ እግዚአብሔርንም፥ 11ስምህንም ለዘለዓለም አመሰግናለሁ፤ 12ከሞትም አዳንኸኝ፤ መከራ ከሚመጣበት ቀንም አዳንኸኝ፥ 13እኔ ሕፃን ሳለሁ ሳልሳሳት ጥበብን መረመርኋት፤ 14በቤተ መቅደስም ስለ እርስዋ ለመንሁ፤ 15ፍሬዋም እንደ ተክል ፍሬ በዛ፤ 16በጆሮዬም ፈጽሜ አደመጥኋት፤ መረጥኋትም፤ 17በእርሷም ከፍ ከፍ አልሁ፤ 18አደርጋትም ዘንድ ዐሰብሁ፤ 19ሰውነቴም በእርሷ ተበረታታች፤ 20ሰውነቴንም ወደ እርሷ አቀናሁ፤ በንጽሕናም አገኘኋት፤ 21ሰውነቴም ለእርስዋ ታወከች፤ መረመረቻትም፤ 22እግዚአብሔርም አንደበትን ዋጋ አድርጎ ሰጠኝ፤ 23እናንት አላዋቂዎች፥ ወደ እኔ ቅረቡ፤ 24እንዴት አጣችኋት? እስኪ ንገሩኝ! 25አፌን ከፍቼ፥ “ያለ ዋጋ ገንዘብ አድርጓት” ብዬ ተናገርሁ። 26አንገታችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ቀንበሯንም ተሸከሙ፤ 27እነሆ፥ ጥቂት ደክሜ በእርሷ ብዙ ዕረፍትን እንዳገኘሁ፥ 28ከብዙ ብር ይልቅ ጥበብን ምረጧት፤ 29ሰውነታችሁም በቸርነቱ ደስ ይበላት፤ 30በጊዜው ዋጋችሁን ይሰጣችሁ ዘንድ፥