ጥበብ ከፍ ከፍ እንደምታደርግ
11ጥበብስ ልጆችዋን ከፍ ከፍ አደረገቻቸው፤ 12እርሷን የወደደ ሕይወቱን ወደደ፤ 13አጥንቶ የሚይዛት ሰውም ክብርን ይወርሳል፥ 14እርስዋንም የሚያገለግሉ ቅዱሱን ያገለግላሉ፤ 15እርስዋን የሚሰማትም አሕዛብን ይገዛል፤ 16ካመንኻት ታገኛታለህ፤ 17ከእርሱ ጋር ትሄድ ዘንድ ትቀድማለች፤ 18ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ተቀብላ ደስ ታሰኘዋለች፤ 19ከእርሷ ወጥቶ ቢስት ግን ትለየዋለች። 20ጊዜውን ጠብቅ፥ 21በማፈር ኀጢአትን የሚሠራ አለና፤ 22ጕዳት በራስህ ስለሚደርስብህ የሰው ፊት አይተህ አታድላ፥ 23የሚናገርን ሰው መናገሩን አትከልክለው፤ 24ጽድቅን አትቃወም። 25ኀጢአትህንም መናገር አትፈር፥ 26ለሰነፍ ሰው ራስህን አታዋርድ፤ 27ፈጣሪህ እግዚአብሔር ስለ አንተ ይከራከርልሃልና 28በአፍህ አውታታ አትሁን፤ 29በቤትህ እንደ አንበሳ አስፈሪ አትሁን፤ 30ለመበደር እጅህን አትዘርጋ።